ድንጋይ ዳቦ ሆነ || በእውቀቱ ስዩም

ድንጋይ ዳቦ ሆነ || በእውቀቱ ስዩም

አንዲት አረጋዊት
ጥቁር ኢትዮጵያዊት
ትመካበት የላት
ባለፀጋ ዘመድ
ፊቷ የለበሰ፤- ፅናት ላብና አመድ
እሷ አለቃ ሆና፤ ክንዶቿን ቀጣሪ
እሱዋ ድሃ ሆና ፤ የሀብታሞች ጧሪ::

እየተጋች አድራ እየለፋች ስትውል
እድሜና ተስፋዋን፤ ያስተሳሰረው ውል
ቢቀጥን ቢሳሳ
ከሸረሪት ፈትል
መሀረብ ዘርግታ
ተዘከሩኝ ሳትል
እንባ ሳታስቀድም፤
ምሬት ሳታስከትል

ፍላጎት ባይኖራት፤ ለውዳሴ ከንቱ
የስራችው ገድል፤ ዜናው ባይሰማ
ይህ ሁሉ ከተማ
ህንፃው ሰገነቱ
የሷን ላብ ጠብቶ ነው፤ የፋፋው ደረቱ ፤

አንዲት አረጋዊት
ጥቁር ኢትዮጵያዊት
በዝምታ ዜማ፤ፅናት የምትዘምር
ይፈልቃል ከጆቿ:፤ እፁብ ድንቅ ተአምር !
መዶሻውን ተነሳ
አቧራው በነነ
በመዳፎቿ ስር ፤ድንጋይ ዳቦ ሆነ!

(ለላብ አድሮች ቀን የተገጠመ)

LEAVE A REPLY