ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በኮሮና የተጠቁ ሰዎች ከዓለም ቀዳሚ መሆኗ ክብር ነው አሉ

ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በኮሮና የተጠቁ ሰዎች ከዓለም ቀዳሚ መሆኗ ክብር ነው አሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአሜሪካው ፕሬዝዳነት ዶናልድ ትራምፕ አገራቸው በኮሮናቫይረስ መያዛቸው በተረጋገጡ ሰዎች ብዛት ከዓለም ቀዳሚ መሆኗ ክብር ሊያሰጣት ይገባል አሉ።

ውዝግብ የማያጣቸው ትራምፕ ዋይት ሐውስ ውስጥ በሰጡት መግለጫ ላይ “ይህንን ነገር በተለየ መልኩ ነው የምመለከተው ፤ የተገኘውን ውጤት እንደ ጥሩ ነገር ነው የማየው። ምክንያቱም ይህ የምናደርገው ምርመራ ከሁሉም የተሻለ መሆኑን ያሳይል” ሲሉ ተደምጠዋል ። በአሜሪካ በአሁኑ ጊዜ 1.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን 92 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሕይወታቸውን እንዳጡ የጆንስ ሆፕኪንስ ዮንቨርስቲ ያወጣው መረጃ ያሳያል።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአሜሪካ ከተከሰተ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰኞ ዕለት የካቢኔ ስብሰባቸውን ያካሄዱት ፕሬዝዳንቱ ለጋዜጠኞች  ሲናገሩ፤ አገራቸው በበሽታው በተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚ የሆነችው ከየትኛውም አገር በበለጠ ምርመራ በማድረጓ መሆኑን ጠቁመው፤ “በርካታ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ሲኖረን፣ በአንድ መልኩ እንደ መጥፎ ነገር አላየውም፤ ምክንያቱም ምርመራችን የተሻለ መሆኑን ስለሚያመለክት” በማለት አስታውቀዋል።

“የተገኘው ውጤትን እኔ እንደ ክብር ምልክት ነው የማየው። በአውነትም የከብር ምልክት ነው። የተገኘው ውጤት በመመርመር እና በተለያዩ የሕክምና መስኮች ላይ የተሠማሩት ባለሙያዎች ላከናወኑት ሥራ የተገኘ ውጤት ነው” ሲሉ ዶናልድ ትራምፕ ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ፤ የተቀናቃኛቸው ዲሞክራቲክ ፓርቲ ብሔራዊ ኮሚቴ ከሪፐብሊካን ፓርቲ የመጡትን ፕሬዝዳንት ባደረጉት ንግግር ክፉኛ ተችቷል። ፓርቲው በትዊትር ገጹ፤ በአሜሪካ 1.5 ሚሊዮን የኮቪድ-19 ህሙማን መገኘታቸው የሚያስከብር ሳይሆን የአመራሩን ፍጹም ውድቀትየሚያመለክት መሆኑንም ገልጿል።

LEAVE A REPLY