በግፍ ሼለቆ ውስጥ || በማሕሙድ እንድሪስ

በግፍ ሼለቆ ውስጥ || በማሕሙድ እንድሪስ

በክፋት አረንቋ መዘፈቃችንን አናውቅም‘ንጂ አምነን
ወንጄል ለመተንተን ቅጣት ለመበየን ማንም አያክለን
በጓዳም በሼንጎ በግልም በቡድን ፍርድ አዋቂወች ነን ።
በአቋሙ ፀንቶ
ወይም ተፀፅቶ
በነፍጥ ተገዶ
ወይ ራሱ ፈቅዶ
አምኖም ይሁን ክዶ
ቅጣቱን ሊቀበል ፊታችን ለቆመ ምህረትም የለን።

እሱንም እኛንም አንተው ይቅር በለን።

LEAVE A REPLY