የትራምፕ ውሳኔ የክትባት ምርምን እንደሚያደናቅፍ የአሜሪካ ጤና ምክር ቤት አስታወቀ

የትራምፕ ውሳኔ የክትባት ምርምን እንደሚያደናቅፍ የአሜሪካ ጤና ምክር ቤት አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ዶናልድ ትራምፕ ከዓለም ጤና ድርጅት አሜሪካን ማግለላቸው የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት ያደናቅፋል ሲሉ የአሜሪካ ምክር ቤት የጤና ኮሚቴ ሓላፊ ገለፁ።
የፕሬዘዳንቱ ውሳኔ ቫይረሶች አሜሪካ እንዳይገቡ ከሌሎች አገራት ጋር የሚደረገውን ትብብር ከባድ ያደርገዋል ያሉት የሪፐብሊካኑ ሴናተር ለማር አሌክሳንደር የትራምፕን ውሳኔ በይፋ ተችተዋል።
“የዓለም ጤና ድርጀት ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የሠራቸው ስህተቶች ካሉ መፈተሽ ተገቢ ነው። ነገር ግን ያ መደረግ ያለበት ወረርሽኙ ካለፈ በኋላ ነው እንጂ በቀውሱ መካከል አይደለም” ሲሉም የአሜሪካው ፕሬዝዳንትን ችኩልነት ተችተዋል።
ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር ግንኙነት ማቋረጥ ውጤት አልባ ነው። ከዚህ የጤና ቀውስ ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት ያከብደዋል እንጂ መፍትኄ አይሆንም ብለዋል፤ የአሜሪካ የጤና ባለሙያዎች ሓላፊ ፓትሪክ ሀሪስ።

LEAVE A REPLY