ድረሱልኝ ይላል! || ዘ-ጌርሣም

ድረሱልኝ ይላል! || ዘ-ጌርሣም

ድረሱልኝ ይላል ድምፅ አውጥቶ እንደሰው

መተንፈስ አቅቶት አየር ስላነሰው

ዓሣና ጉማሬው አዕዋፋት በሙሉ

እምቦጭ ረግጧቸው ታፍነዋል አሉ

ምን ዓይነት ዘመን መጣ?

ትውልድን በጅምላ የሚቀጣ

የፈጣሪ ወይስ የተፈጥሮ ቁጣ

ጣናን የሚያክል ያገር ሀብት

በወረርሽኝ ተጠቅቶ ማየት

ለማነው? አቤት የሚባለው

ቀጥተኛ ሃላፊነት ያለው

ህዝቡ ወይስ መንግሥት ?

አለሁ የሚል ፊት ለፊት

ፖለቲከኛው ወይስ ምሁ?

የሚኮፈሰው በሀገርሩ

ቢታደልማ ኑሮ

ዙሪያ ገቡ አምሮ

ለቱሪስት ተመቻችቶ

የውጭ ምንዛሬ አስገኝቶ

ኑሮም በተሻሻላለ

ከልመናም በተዳነ

ምነው ጣና! ምነው አባይ!

የሆንክብን ለኛ ስስት ለባዕድ ሲሳይ

ጣና ማለት እኮ አባይ ነው

መነሻና መፍለቂያው

ጣና ተጎዳ ማለት

ንጥፈት አኮ ነው ለአባይ ፍሰት

 

ተከናንቦ ቢያርሱ

በአረም ይመለሱ

ብሎ ይተርታል

ነገር ይደርታል

ለመላጣ እራሱ በሚዶ ይጣላል

የራሱን አቃጥሎ የሰው ቤት ይመኛል

አቤት! አቤት በሉ ምህላ ገብታችሁ

አላህ ወአክብር ሉ ዱዓ ላይ ያላችሁ

ይሁን ፀሎታችሁ ሌም ምኞታችሁ

በዕምነት ለፈጣሪ ስለቀረባችሁ

የጣና ሆድ ሕመም ለአባይ ቁርጥማት ነው

ቁማር ለተበላ ውጤቱ ዜሮ ነው

ሮ ከዜሮ ጋር ከተደማመሩ

በዜሮ ይዘጋል የሂሣብ ቀመሩ

የታሉ ? ምሁራን

የታሉ ? ሊቃውንት

የት ነው ፖለቲካው

ማነውስ ትላኪው

ይህን ጉድ እያዩ

መለየት ያልቻሉ ምድርን ከሰማዩ

ጭራሽ አልሰማሁም

ምንም አላየሁም

ጀሮዬን ይድፈነዉ

ዓይኔንም ያውረው

ብለው የሚምሉ

ጊዜ የሌላቸው ሁልጊዜ ስብሰባ

ጣናን ያጋለጡ ለጥቃት ሰለባ

የጣና መጠቃት ጉዳዩ የማነው?

የፌደራል ድርሻ ወይስ የክልል ነው

የታለ? ሚዲያው ምንጫችን የወሬው

ሰበር በሚል ዜና ናላ የሚያዞረው

ምነው! ተጠየፉት የጣናን መጎዳት

ህዝብ እንኳን አንዳያውቅ ዕድል የነፈጉት

ሰበር ስሚ ዳኛ ካልተሰየመለት

ታሪክ ያበላሻል የጣና መጎዳት

ትውልዱ እሚከፍለው  ትልቅ ዕዳ አለበት

                               

                               2020-06-21

LEAVE A REPLY