ፕ/ት ትራምፕን “ያሳፈሯቸው” ወ/ሮ ሜሪይ ማናቸው? || (ታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ

ፕ/ት ትራምፕን “ያሳፈሯቸው” ወ/ሮ ሜሪይ ማናቸው? || (ታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ

የአሜሪካው ፕ/ት ዶናል ትራምፕ ባለፈው ቅዳሜ በኦክላሀማ ግዛት ያካሄዱት የምርጫ ቅስቀሳ በቅድሚያ ብዙ ደጋፊዎች ይታደማሉ ታብሎ ብዙ ቢነገርለትም በገሃድ የታየው ግን በጣም አንስተኛ የ ደጋፊዎች ተሳትፎ ነበር የተስተዋለበት። እንደ በርካታ ሚዲያዎች ዘገባ ለዚህ ታላቅ የፖለቲካ ክስረት አንዲት ሴት ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን ይናገራሉ።

እንደ እነዚህ ዘገባዎች እምነት የኦሃዮ ግዛት ነዋሪ የሆኑት የሀምሳ እንድ አመቷ ሜሪይ ጆ ላኣፕ በወዳጆች መረብ ቲክ ቶክ(Tik Tok) አማካኝነት ከሁለት ሳምንት በፊት የትራምፕን የቅዳሜ እለቱ የምርጫ ቅስቀሳን በደጋፊዎች እንደሚያ ጥለቀልቁት በማስመሰል ቪዲዮ በመክፈት ለቀናት ጠበቁ ።በመምህርነት ስራ የሚተዳደሩት ሜሪይ ለትራምፕ የቅስቀሳ ዘመቻ ላይ የሚመዘገቡ ሰዎች ኢሚል፣ሙሉ ስም እና የስልክ እድራሻ ስላሚጠይቁ የስልክ ቀጥራቸውን የውሸት ወይም ጊዜያዊ ቁጥር በመስጠት ለአዳራሹ ለመግባት እንዲመዘገቡ አደረጉ።

ፕ/ት ትራምፕ ሳይቀሩ ብዙ ያወሩለት፣ ዙርያ ገባው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ታዳሚዎች እንደሚገኙ ያወሩለት የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ ላይ አስራ ዘጠኝ ሺህ በሚይዘው ስታዲዮም ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ብቻ ሲገኙ የተቀሩት ተመዝጋቢዎች ዝር ሳይሉ ቀርተዋል።
እጩ ዲሞክራቱ ጆኦ ባይደንን ስለመምረጣቸው ገና ያልወሰኑት፣ባለፈው እኤአ 2016 ትራምፕን ያልመረጡት ወ/ሮ ሜሪይ ከሲኤን ኤን ቴሌቭዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “እንደ አሜሪካ ዜግነታችን ወጣቱ ትውልድ መምረጥ እንኳን ባይችሉ በመህብራዊ ሚዲያ አማካኝነት ተቃውሟቸውን እንዴት መግለጽ እንዳላባቸው፣ ድምጻቸውን እንዴት ማሰማት እንደሚችሉ ልናስተምራቸው ግድ ይለናል፣የተደረገው ዘመቻ እንጂ ማሞኘት/ፕራንክ አይደለም” ብለዋል።

የትራምፕ የምርጫ ዘመቻ አስተባባሪዎች ከስምንት መቶ ሽህ በላይ ሰዎች መመዝገባቸውን እና ይህም ቁጥር በምርጫ ቅስቀሳ ታሪክ ውስጥ ትልቁ መሆኑን ቢናገረሩም የታዳሚዎቹ ቁጥር እንደዚህ በእጅጉ ያሽቆቃለቆለበት ምክንያት “በሚዲያዎች የቅስቀሳ ዘመቻ ሳቢያ ነው” በማለት አስተባብለዋል።

ያ ከአንድ ሺህ በላይ ተከታዬች ያልነበሩት የሜሪይ ቪዲዬ በአንድ ምሽት ከሁለት ሚሊዬን በላይ ሰዎች ተመልክተውታል። ከሰባት መቶ ሽህ በላይ ድጋፋቸውን (like) አድርገውታል፣ ስንት ሰዎች እንደተጋሩት በእርግጠፕኝነት መናገር ቢከብድም፣ በሚሊዬን የሚቀጠር ተከታይ ያላቸው ሰዎች ተጋርተውታል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋትን ሳይግፈፈፍ ፣የህክምና ባለሙያች ምክርን ወደጎን በመተው” የፈለገ ሰው የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም ይችላል” የሚል መመሪያ በመስጠት ደጋፊዎች ማህበራዉ መራራቅን ተግባራዊ ሳያደርጉ ወደ ቱስላ ፣ኦክላሃማ እንዲመጡ ያደረጉት፣ በወረርሽኙ ሁለት የቅስቀሳ አባላት የተጠቁባቸው፣ጥቁሮች ከባርነት በይፋ ነጻ መውጣታቸው የታወጀበት በሚከበርለት ታላቅ እለት የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ ያካሄዱት ፣ሚኒሶታ ላይ በነጭ ፖሊሶች በግፍ ስለተገደለው ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ እና የፍትህ እጦት ምንም ያልትናገሩት ፕ/ት ትራምፕ በርካታ ትችች ቢቀርብባቸውም በስታዲዬሙ የታደሙት ደጋፊዎቻቸው ከመቼውም ጊዜ በብዛት መምጣታቸውን በመግለጽ “አርበኞች” ብለዋቸዋል።

LEAVE A REPLY