ፖሊስ እስክንድር ነጋንና ሸምሰዲን ጠሃን የደበደብኩት ሲያዙ ግብግብ ስለገጠሙኝ ነው ማለቱን ዶ/ር...

ፖሊስ እስክንድር ነጋንና ሸምሰዲን ጠሃን የደበደብኩት ሲያዙ ግብግብ ስለገጠሙኝ ነው ማለቱን ዶ/ር ዳንኤል ተናገሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ዶክተር ዳንኤል  በቀለ ከሁለት ሳምንት በፊት በተለያዩ ቦታዎች ላይ የተከሰተውን ለሰዎች ሞትና ለንብረት ውድመት የሆነውን ክስትት ጋር በተያያዘ የደረሱ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶችን እያጣሩ መሆናቸውን አስታወቁ።

የተፈፀመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዓይነት እና የጉዳት መጠን ለይቶ ለማወቅ፣ በተጨማሪም አጥፊዎቹ በሕግ እንዲጠየቁ፣ የተጎዱ ሰዎች ደግሞ እንዲካሱና መልሰው እንዲቋቋሙ ለማስቻል የሚረዳ ጥናት ለማካሄድ አንድ ቡድን መቋቋሙን ዋና ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።
አሁንም ሙሉ ፀጥታና መረጋጋት ያልሰፈነባቸው አካባቢዎች ላይ፣  አልያም ጉዳቱ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በፀጥታ ኃይሎች የተወሰደው ሕግ የማስከበር እርምጃ፤ ከተፈጠረው ችግር ጋር ምን ያህል ተመጣጣኝ እንደሆነ ለማጣራት ዝግጅት መጀመሩን የጠቆሙት ዶክተር ዳንኤል፤ ከኹከቱ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎች አያያዝ ሕጋዊነትን ለማወቅ ክትትል እያደረጉ እንደሚገኙም ይፋ አድርገዋል።
ከተፈጠረው ኹከት ጋር ተያይዞ መንግሥት የሰጠውን ምላሽ በተመለከተ ጥናት እያደረጉ እንደሆነ፣ እስካሁን ባላቸው ቅድመ ምልከታና መረጃ መሠረትም በአብዛኛው የፀጥታ አስከባሪዎች ሚና ሰላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን እና የፀጥታ አካላት ባይደርሱ ኖሮ ጉዳቱ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ግንዛቤ መገኘቱንም ሓላፊው አስረድተዋል።
 “የፀጥታ አካላት ሕብረሰተቡን ለመጠበቅ በወቅቱ አልደረሱም” የሚል በርካታ አስተያየት እንጂ በፀጥታ አስከባሪዎቹ ጉዳት ደረሰብን የሚል አይደለም ያሉት ኮማሽነር ዳንኤል በቀለ፤ አልፎ አልፎ የፀጥታ ኃይሎች ሕግ በማስከበር ሂደት ላይ ስህተት መፈጸማቸውን የሚያረጋግጥ መረጃም አለን ብለዋል።
ጉዳዮ ከተጣራ በኋላ ያጠፋ አካላት (በየትኛውም እርከን ላይ የሚገኙ ቢሆንም) በሕግ እንዲጠየቁ፣ የተጎዱም እንዲካሱ እናደርጋለን ያሉት የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር በእስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኞችን አያያዝ በተመለከተም በአካል ተገኝተው እንደጎበኙ ተናግረዋል።
እስክንድር ነጋና የኦ ኤም ኤኑ ጋዜጠኛ ሸምሰዲን ጠሃ በተያዙበት ወቅት ድብደባ እንደተፈጸመባቸው የነገሯቸው መሆኑን ያስታወሱት የጸጥታ አካላቱ ለምን ግለሰቦቹን እንደደበደበ ከፖሊስ አመራሮች ጋር በተወያዮበት ወቅት “ስንያዛቸው ግብግብ በመፈጠሩ ነው ድብደባ የፈጸምነው” የሚል ምላሽ እንደተሰጠቸው ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY