ሀጫሉን ኢንተርቪ ያደረገው የኦ ኤም ኤን ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮ ዛሬ መታሰሩ ታወቀ

ሀጫሉን ኢንተርቪ ያደረገው የኦ ኤም ኤን ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮ ዛሬ መታሰሩ ታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ሀጫሉ ሁንዴሳ ከመገደሉ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ቃለምልልስ ያደረገለት የኦ ኤም ኤን ጋዜጠኛ የሆነው ጉዮ ዋሪዮ ዛሬ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ ተሰማ።

የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አባላት ዩኒፎርም የለበሱ የጸጥታ አካላት ግሰቡን ዛሬ ምሳ ሰዐት አካባባ ከመኖሪያ ቤቱ ይዘውት እንደሄዱ ቤተሰቦቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የቤተሰቡ አባላት  የጸጥታ አባላቱ ጉዮን የት ይዘውት እንደሚሄዱ ለመናገር ፍቃደኛ እንዳልነበሩም ገልጸዋ።
 ቀደም ሲል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሀጫሉን ግድያ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ላይ፤ ድምጻዊው ከኦኤም ኤን ጋር ያደረገው ቃለመጠይቅ የ1 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ርዝመት ቢኖረውም ፣ ሆን ተብሎ ብሎ አንዳንድ ክፍሎቹን ተቆርጦ እንዲወጣ ተደርጓል ማለቱ አይዘነጋም።
በኦኤምኤን ላይ ተላለፈው የድምጻዊ ሃጫሉ ቃለ መጠይቅ ጠቅላላ ርዝመት 47 ደቂቃ ብቻ ሲሆን፣ በዐቃቤ ሕግ መግለጫ መሠረት ተቆርጦ የወጣው ቃለመጠይቅ ድምጻዊው ከኦነግ ሸኔ የሚደርስበትን ዛቻ የገለጸበት ክፍል ነው።
ከቀናት በፊት ሌላኛው የኦኤምኤን ጋዜጠኛ የሆነው መለሰ ዲሪብሳ በቁጥጥር ስር መዋሉ የተረጋገጠ ሲሆን፤  የኦኤምኤን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ግርማ ጉተማ ሚዲያው ከተዘጋ በኋላ “ጋዜጠኞቹ በስጋት ስልካቸውን አጥፍተው ተደብቀዋል” ሲሉ መናገራቸውም ይታወሳል።

LEAVE A REPLY