በእነ ጃዋር መሐመድ ላይ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ዛሬ መሰማት ጀመሩ

በእነ ጃዋር መሐመድ ላይ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ዛሬ መሰማት ጀመሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ዐቃቤ ህግ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14 ተጠርጣሪዎች ላይ ዘጠኝ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን  አቀረበ።

15 የቅድመ ምርመራ ምስክሮች ማዘጋጀቱን የገለፀው ዐቃቤ ህግ ፤ ከ15 ምስክሮች ውስጥ አራቱ በተለያዩ ምክንያቶች እና የምስክር ጊዜ ላለማራዘም  ማሰማት አልፈልግም ሲል ለችሎቱ አስረድቷል።
ዐቃቤ ህግ በ11ኛ እና 14ኛ ተራ ቁጥር ያስመዘገባቸው ቀሪ ሁለት ምስክሮች ስልካቸው ባለመሥራቱ ለነሃሴ 29 ቀን 2012 ዓ.ም ከመጋረጃ በስተጀርባ ምስክርነት ይሰማልኝ በማለት ፍርድ ቤቱን መጠየቁም ታውቋል።
በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የተገኙት አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ የዐቃቤ ህግ ቀሪ ሁለት ምስክሮች ዛሬ ተደምጠዋል።
ይህን ተከትሎ  ዐቃቤ ህግ የሚያሰማቸው እና የማያሰማቸው ቀሪ ምስክሮች ዝርዝር ይገለፅልን ሲሉ የተጠርጣሪ ጠበቆች ቢጠይቁም፤ ዐቃቤ ህግ በበኩሉ ለደህንነታቸው ሲባል ዝርዝራቸውን አልገልፅም፤ ከዚህ በፊት ምስክር የነበሩ ግለሰብ በተተኮሰባቸው ሽጉጥ ጉዳት ደርሶባቸው ፓሊስ ጣቢያ ማደራቸውን አድረዋል። በተለያዩ ጊዜ ምስክሮች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰ በመሆኑ ለደህንነታቸው ስል ዝርዝራቸውን መግለፅ አልፈልግም” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
አቶ በቀለ ገርባ የባንክ ሂሳባቸው መታገዱን፣ የግል ተሽከርካሪያቸውም እንዳልተመለሰላቸው አቤቱታ አቅርበው፤ በተጨማሪነት የማረሚያ ቤት አያያዛቸው እንዲስተካከል ጥያቄ አቅርበዋል።
አቶ ሃምዛ አዳነ (ቦረና)  በአንድ መጽሔት እንዲሁም በሌሎች ጋዜጦች ስሜ እየጠፋ ነው ሲሉ አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን፤ አቶ ሸምሰዲን ጠሃ የተባሉ ተጠርጣሪም የጆሮአቸውን ህመም በሚፈልጉት የህክምና ተቋም እንዲታከሙ ፍርድ ቤቱ ያዘዘው ትዕዛዝ አልተፈፀመም ሲሉ ዳግም አቤቱታ አቅርበዋል።
 ፍርድ ቤቱም በተነሱ አቤቱታዎች ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት እና ሁለት የዐቃቤ ህግ ከመጋረጃ ጀርባ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት ለነሀሴ 29 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል።

LEAVE A REPLY