አቶ ደመቀ መኮንን ህወሓትን አስመልክቶ በውጭ ከሚገኙ የኢፊዲሪ ሚሲዮን መሪዎች ጋር ተወያዮ

አቶ ደመቀ መኮንን ህወሓትን አስመልክቶ በውጭ ከሚገኙ የኢፊዲሪ ሚሲዮን መሪዎች ጋር ተወያዮ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በም/ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን የህግ ማስከበር ዘመቻን በተመለከተ በውጭ ከሚገኙ የኢፌዲሪ ሚሲዮን መሪዎች ጋር ውይይት አካሄዱ።
በህግ ማስከበር ዘመቻው ሲቪሎች እንዳይጎዱ ተገቢው ጥንቃቄ በማድረግ እንደሆነ የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፤ ከህወሓት ጁንታ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ለማኅበረሰቡ የሰብኣዊ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አቶ ደመቀ ገልጸዋል።
የሚሲዮን ሓላፊዎችና ሁሉም ዲፕሎማቶች መንግሥት በጁንታው ላይ የሚያካሂደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ በተመለከተ ለቀጣናዊና ዓለም ዐቀፍ ማኅበረሰብ የማስገንዘብ ተግባራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም በተካሄደው ውይይት ላይ ም/ጠ/ሚርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል።

LEAVE A REPLY