ከመቀሌ በስተሰሜን የምትገኘው እዳጋ ሐሙስ ከተማን መከላከያ ሠራዊቱ ተቆጣጠረ

ከመቀሌ በስተሰሜን የምትገኘው እዳጋ ሐሙስ ከተማን መከላከያ ሠራዊቱ ተቆጣጠረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከትግራይ ዋና ከተማ መቀለ በስተሰሜን የምትገኘውን እዳጋ ሐሙስ የተባለችውን ከተማ መከላከያ ሠራዊቱ  መቆጣጠሩ ታወቀ።

የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ ጽ/ቤት እዳጋ ሐሙስ ከአዲግራት ወደ መቀለ በሚወስደው መስመር ላይ የምትገኝ ከተማ መሆኗን ጠቁሞ፤ ትናንት በትግራይ ክልል ሁለተኛ ከተማ የሆነችው የአዲግራት ከተማ በኢትዮጵያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር ሙሉ ለሙሉ መዋሏን አስታውሷል።
እዳጋ ሐሙስ ከክልሉ ዋና ከተማ መቀለ 116 ኪሎ ሜትሮች ያህል ርቃ ከምትገኘውና የምሥራቃዊ ትግራይ ዞን ማዕከል ከሆነቸው አዲግራት ከተማ ቀጥላ የምትገኝ ወሳኝ ቦታ በመሆኗ የጁንታውን ቡድን ለመቆጣጠር አመቺ ሁኔታ መኖሩ በስፋት እየተነገ ይገኛል።

LEAVE A REPLY