የእግር ኳሱ ፈርጥ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

የእግር ኳሱ ፈርጥ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በፊፋና በሕዝብ የዓለማችን የምንጊዜም ምርጡ ኮከብ ተጨዋች ሆኖ የተመረጠው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ዛሬ በ60 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

የኳስ ፈርጡና የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ማራዶና ከቀናት በፊት ከሆስፒታል ከህመሙ አገግሞ የወጣ ቢሆንም ዛሬ ህይወቱ አልፏል፡፡
ማራዶና ከሁለት ሳምንታት በፊት ጭንቅላቱ ውስጥ ባጋጠመው የደም መርጋት ምክንያት ወደ ሆስፒታል ተወስዶ በጭንቅላቱ ላይ የቀዶ ሕክምና የተደረገለት ቢሆንም፤ ዛሬ በልብ ህምም ምክንያት ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል።

LEAVE A REPLY