በሰላም ሚኒስቴር ስር የሰብኣዊ እርዳታ አቅርቦት መተላለፊያ ቦታ መንግሥት ሊያመቻች ነው

በሰላም ሚኒስቴር ስር የሰብኣዊ እርዳታ አቅርቦት መተላለፊያ ቦታ መንግሥት ሊያመቻች ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ መንግሥት የሰላም ሚኒስቴር የሚከታተለው የሰብኣዊ እርዳታ አቅርቦት መተላለፊያ ቦታ የኢትዮጵያ መንግሥት ሊያመቻች ነው ተባለ።

በትግራይ ክልል የሰብኣዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸውን ዜጎች እገዛ እያደረገ መሆኑን ዛሬ በመግለጫው ያረጋገጠው የኢትዮጵያ መንግሥት፤ ምግብ፣ መድኃኒት፣ ውሃና አስፈላጊ የሚባሉ መሰረታዊ የእርዳታ አቅርቦቶችንም የፌደራል መንግሥት በተቆጣጠራቸው የትግራይ ክልል አካባቢዎች በመቅረብ ላይ መሆናቸውንም አስታውቋል።
ግጭቱን ፈርተው ወደ ሱዳን ለሸሹት ሰዎች መጠለያ ካምፖች እንደሚያቋቁም የተናገረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት፤ በተጨማሪም በግጭቱ ሳቢያ ተፈናቅለው ወደ ቀያቸው ለመመለስ የሚፈልጉትን ዜጎች ለመርዳት ዝግጁ መሆኑን ጠቁሞ፣ እቅዱን እውን ለማድረግ ብሎም የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅና ለመደገፍ ከእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ጋር ተባብሮ ለመሥራት ፍላጎቱ አለኝ ብሏል።

LEAVE A REPLY