አራት ክልሎች በተሽከርካሪ ምርመራ ጥራት ማረጋገጫ አሰጣጥ ላይ ስህተት ይታይባቸዋል ተባለ

አራት ክልሎች በተሽከርካሪ ምርመራ ጥራት ማረጋገጫ አሰጣጥ ላይ ስህተት ይታይባቸዋል ተባለ

ADDIS ABABA, ETHIOPIA - APRIL 4 : Ethiopian Transport Minister Dagmawit Moges speaks during a press conference on "Boeing 737 Max 8" crash in Addis Ababa, Ethiopia on April 4, 2019. (Photo by Minasse Wondimu Hailu/Anadolu Agency/Getty Images)
 ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከተሽከርካሪ ምርመራና ብቃት ማረጋገጫ ሰርቸፍኬት አሰጣጥ አገልግሎት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው አራት ክልሎች የሥራ ጥራት ችግር በግልጽ ይታይባቸዋል ተባለ።
አደረግኹት ያለውን ጥናት ተከትሎ የትራንስፖርት ሚኒስቴር በአራት ክልሎች እና አንድ የከተማ አስተዳደር በተሸከርካሪ ምርመራ ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ተቋማት የሥራ ጥራት ችግር ያለባቸው መሆኑንና በትክክል ያልተረጋገጠ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እየሰጡ መሆናቸውን ገልጿል።
በኢትዮጵያ 95 በመቶ የሚሆነው የተሽከርካሪ ምርመራ የሚያደርጉ ተቋማት አዲስ አበባ ፣ ኦሮሚያ ፣ ደቡብ ብሔር ብሔረሶች እና ሕዝቦች ፣ ትግራይ እና አማራ ክልል የሚገኙ ሲሆን ፤ 41 በሚሆኑ የተሽከርካሪ ምርመራ በሚያካሂዱ ተቋማት ላይ በትራንስፖርት ሚኒስቴር በተደረገው ጥናት መሠረት አራት ክልሎችና አንድ ከተማ አስተዳደር በአግባቡ ምርመራ እንደማያደርጉ ተረጋግጧል።

LEAVE A REPLY