አቶ ልደቱ አያሌው ነገ ዳግመኛ ሊታሰሩ ይችላል እየተባለ ነው

አቶ ልደቱ አያሌው ነገ ዳግመኛ ሊታሰሩ ይችላል እየተባለ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || “መንግሥትን በኃይል ለማፍረስ ሞክረዋል” የሚለው የአቶ ልደቱ አያሌው ክስ ፤ ያስከስሳል ወይንም አያስከስስም የሚለውን ለመበየን ዛሬ ችሎት የተሰየመው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስከስሳል ሲል ብይን ሰጥቷል።

የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡት አቶ ልደቱ አያሌው፤ “ሊያስከስሰኝ አይገባም፣ ወንጀሉንም አልሰራሁም ከማለታቸው ባሻገር እንዲህ ያሉበትን ምክንያት በዝርዝር በማስረዳት ቃላቸውን ለችሎቱ ሰጥተዋል፡፡
ነገ በኦሮሚያ ምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት “ህገ ወጥ መሳሪያ ይዞ በመገኘት” የሚለው ክሳቸው በሌላ መዝገብ የሚታየው ዛሬ ከታየው የፍርድ ቤት ውሎ አኳያ ሊፈረድባቸው እና ወደ እስር ቤት ሊመለሱ እንደሚችሉም ስጋት እንዳደረባቸው የቅርብ ሰዎቻቸው ገልጸዋል።
በፍርድ ቤቶች ተስፋ የቆረጡት አቶ ልደቱ አያሌው ከወዲሁ “የመሳሪያ ክሱን እንደ እልህ መወጣጫ ቆጥረው ሊፈርዱብኝ ይችላሉ” ሲሉ ለፓርቲያቸው የቅርብ ሰዎችና ለቤተሰቦቻቸው መናገራቸውም ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY