የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር “በማህበር ተደራጅተው ቤት ለሚሰሩ መሬት አዘጋጅቻለሁ” አለ!

የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር “በማህበር ተደራጅተው ቤት ለሚሰሩ መሬት አዘጋጅቻለሁ” አለ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበማህበር ተደራጅተው ቤት ለመገንባት በመመዝገብ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች በአምስት ክፍለ ከተሞች መሬት ማዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ቢሮ አስታወቀ።

“በከተማዋ የሚታየውን ሰፊ የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ አማራጮችን ይዤ እየተንቀሳቀስኩ ነው” ያለው ቢሮው፣ በ20/80 እና በ40/60 ፕሮግራም ሙሉ ክፍያ ከፍለው ቤት ለማግኘት እየተጠባበቁ ላሉና 70 በመቶ መክፈል ለሚችሉ ነዋሪዎች፤ በማህበር ተደራጅተው መኖሪያ ቤት መገንባት የሚችሉበትን አማራጭ ይዞ መቅረቡን አስታውቋል።

በመጀመሪያ ዙር ከ100 እስከ 130 ማህበራት ለማደራጀትና 10 ሺህ የሚደርሱ ቤት ፈላጊ አባወራዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ያመለከተው ቢሮው “ለግንባታው የሚሆን መሬት በአዲስ ከተማ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በኮልፌ ቀራንዮና በቦሌ ክፍለ ከተሞች ተዘጋጅቷል” ሲልም ገልጿል።

ምዝገባው በተጀመረ በአራት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ3000 በላይ ሰዎች መመዝገባቸው ተመልክቷል።

LEAVE A REPLY