ምርጫ ቦርድ የተረጋገጡና ችግር የሌለባቸው ውጤቶችን ዛሬ ይፋ እንደሚያደርግ ገለጸ!

ምርጫ ቦርድ የተረጋገጡና ችግር የሌለባቸው ውጤቶችን ዛሬ ይፋ እንደሚያደርግ ገለጸ!

 

ኢትዮጵያ ነገ ዜናብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰጠው መግለጫ፣ የ618 የምርጫ ክልሎች ውጤት ወደ ማዕከል መድረሱን ገልጾ፣ ፓርቲዎች ካቀረቡት ቅሬታ ጋር በተያያዘ አፋጣኝ መልስ ለመስጠት በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ ከፓርቲዎች ጋር ውይይት ማድረጉን አመልክቷል።

ዛሬ አመሻሽ ላይ በስካይ ላይት ሆቴል በተጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ “ፓርቲዎቹ ካቀረቧቸው ከቅሬታቸው ጋር በተያያዘ ቦርዱ የህግ ድጋፍ ለመስጠት ተዘጋጅቷል። ከነገ ጀምሮ የፓርቲዎቹን አቤቱታዎች ማየት ይጀምራል። በሁለት ሶስት ቀናትም መልስ ለመስጠት እንሰራለን” ያሉት የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ “ቦርዱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ዛሬ የተረጋገጡና ችግር የሌለባቸውን ውጤት ያሳውቃል” ሲሉም ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY