በቨርጂኒያ ግዛት በሚካሄደው ምርጫ ኢትዮጵያውያን ዘመቻ ጀምረዋል

በቨርጂኒያ ግዛት በሚካሄደው ምርጫ ኢትዮጵያውያን ዘመቻ ጀምረዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበቨርጂኒያ ግዛት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የጆ ባይደን አስተዳደር የተሳሳተ አካሄድን በቨርጂኒያ በሚካሄደው ምርጫ ለመቅጣት እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

በቨርጂኒያ ምርጫ ላይ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት ለማስቆም ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን የጆ ባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ በሚከተለው የተሳሳተ ፖሊሲ ምክንያት የዴሞክራት ፓርቲን በምርጫው ለመቅጣት እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ በመግባትና አላስፈላጊ ጫና በማድረስ ላይ የሚገኘውን የዴሞክራት ፓርቲ ፖሊሲና የጆ ባይደን አስተዳደር የተሳሳተ አካሄድን በመቃወም ኢትዮ አሜሪካውያን በሰፊው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የዋሽንግተን ፖስት ዘገባ ያመላክታል፡፡

ዋሽንግተን ፖስት ይዞት በወጣው ዘገባ እንዳመላከተው የዴሞክራት ፓርቲንና የባይደን አስተዳደርን በቅርቡ በቨርጂኒያ ግዛት በሚካሄደው ምርጫ ዲሞክራቶችን ለመቅጣት በቨርጂኒያ የሚገኙ ኢትዮ አሜሪካውያን ወደ ተግባር መግባታቸውን ጠቁሟል፡፡

LEAVE A REPLY