በአትላስ ሆቴል ለሶስት ዓመታት አልጋ ተከራይቶ የሽብር ድርጊት ሲፈጽም የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር...

በአትላስ ሆቴል ለሶስት ዓመታት አልጋ ተከራይቶ የሽብር ድርጊት ሲፈጽም የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 በሚገኘው አትላስ ሆቴል ውስጥ ለሶስት ዓመታት አልጋ ተከራይቶ የሽብር ድርጊት ሲፈጽም የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ።

የኢዜአ ምንጮች እንዳመለከቱት ተጠርጣሪው ከሽብርተኛው ሸኔ ጋር በህቡዕ በመገናኘት ተልዕኮዎችን ሲያስተባብር ነበር፡፡

ተጠርጣሪው ባረፈበት ሆቴል ውስጥ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ አደንዛዥ ዕፅ፣ ሶስት ኮምፒዩተሮች፣ ሁለት ፕሪንተሮች፣ ሰባት የተለያዩ ማህተሞች፣ አንድ ላፕቶፕ እና አንድ ትልቅ ማይክ ተገኝቷል።

እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያዎች ለመልቀቅ ያዘጋጀቸው የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ሰነዶች ከሁለት ግብረአበሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ምንጮች አመልክተዋል።

LEAVE A REPLY