አርቲስት ታማኝን ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦችና ቀድሞ ሠራዊት አመራሮች ወደ ግንባር ዘመቱ

አርቲስት ታማኝን ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦችና ቀድሞ ሠራዊት አመራሮች ወደ ግንባር ዘመቱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜናአርቲስት ታማኝ በየነ እና የፖለቲካ ተንታኝና ጸሐፊ አንዳርጋቸው ፅጌን ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦች እና የኢትዮጵያ ቀድሞ ጦር ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ወደ ግንባር ዘመቱ።

ፖለቲከኛ ነዓምን ዘለቀ እና ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳም ወደ ግንባር ከዘመቱት መካከል ይገኙበታል።

በኢትዮጵያ ያጋጠመውን የኅልውና ዘመቻ በተለያየ መንገድ ከፊት ሆነው ሲታገሉ የነበሩ አርቲስቶች እና የቀድሞ ሠራዊት የጦር አመራሮች የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ግንባር መዝመትን ተከትሎ እነሱም እንደሚዘምቱ ከዚህ ቀደም ቃል ገብተው ነበር።

በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የኅልውና አደጋ ለመመከት ዛሬ ወደ ግንባር መዝመታቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

LEAVE A REPLY