ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰተዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚንስትሩ አንደገለፁ አይደለም ኢትዮጵያ ታላላቅ የአለም ኃያል ሃገራት ጦርነት እንደማያዋጣችው በመረዳት፤ በአንድ እጃቸው ጥንቃቄን በአንድ እጃቸው የድርድር ሃሳብን በመያዝ በሃገር እና በህዝብ መካከል ሰላምን ለማምጣት ይጓዛሉ፤ ኢትዮጵያም ይህን ልታደርግ ይገባታል” ብለዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከህውሀት ጋር ድርድር ይደረጋል በሚባለው ጉዳይ ላይ እርሶ ምን ይላሉ ብለው የምክር ቤት አባል ለተጠቁት ጥየቄ ፤ጠቅላይ ሚንስተሩ ‘‘አለማችን ከ3ሺ 500 አመታት ውስጥ ያለ ግጭት በሰላም ያሳለፈቸው 265 አመታትን ብቻ ነው ያሉት፡፡
በተሰራው ጥናት መሰረት በአለማችን ላይ በ3 ሺ 500 መቶ አመታት ውሰጥ 1450 ጦርነቶች መደረጋቸውን አንስተዋል፡፡

‘ከተደረጉ 1450 ጦርነቶች መካከል 215 ጦርነቶች ወታደራዊ ግጭቶች ናቸው ያሉ ሲሆን፤ በነዚህ አመታት ውስጥ በተደረጉ ግጭቶች ምክኒያት 3.4 ቢሊዮን ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል” ነው ያሉት ፡፡

‘‘በኢትዮጵያም በርካታ የግጭት ታሪኮች አሉ፤ በተለይ ባለፉት 34 አመታት የተደረጉ ጦርነቶች ሃገሪቱን በኢኮኖሚ ደክማ እንድትቀር የሚያደርጋት ከመሆኑም በዘለለ፤ በህዝቦች መካከል መለያየትን የፈጠረ ነበር ፤ ለዚህም ማሳያ ኤርትራን መጥቀስ ይቻላል ” ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከፓርላማ አባላት በቅርቡ በምህረት ስለተለቀቁት እስረኞች በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ እስረኞችን የፈታነው በሶስት ምክንያቶች ነው ሲሉም ምላሽ ሰተዋል፡፡

ለዘላቂ ሰላም፤የታሳሪዎችን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ያገኘነውን ድል ለማፅናት እስረኞችን ፈተናል ብለዋል፡፡፡

ከህወሃት ጋር በተያያዘም እስካሁን ምንም አይነት ድርድር አልተደገም ሲሉም ምላሽ ሰተዋል፡፡ ነገር ግን ይህ ማለት እስከመጨረሻው ድርድር አይኖርም ማለት አይደለም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ መንግሥታቸው በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው የመመለሱን ዕቅድ ያዝ ያደረገው በጸጥታ ስጋት እንደሆነ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ተናግረዋል።

ዐቢይ በሳዑዲ ካሉት ታሳሪዎች መካከል ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ስለመሆናቸው እና በቀጥታ ከኢትዮጵያ ወደ ሳዑዲ የሄዱት ስንቶቹ እንደሆኑ ማረጋገጫ እንደሌለ፣ አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ፓስፖርት እንደሌላቸው እና የሰለጠኑ ነፍሰ ገዳዮችም ከመካከላቸው አሉበት የሚል መረጃ መኖሩን ጠቁመዋል። በሕገወጥ መንገድ ሳዑዲ የገቡ ኢትዮጵያዊያንን ጉዳይ መከታተል ለመንግሥታቸው ፈተና እንደሆነበትም ጠቁመዋል።

LEAVE A REPLY