እናት ፓርቲ መንግሥት ሰሞኑን እየወሰደ ባለው የሕግ ማስከበር ርምጃ አመራሮች ታሰሩብኝ አለ

እናት ፓርቲ መንግሥት ሰሞኑን እየወሰደ ባለው የሕግ ማስከበር ርምጃ አመራሮች ታሰሩብኝ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || እናት ፓርቲ መንግሥት ሰሞኑን እየወሰደ ባለው የሕግ ማስከበር ርምጃ በአማራ እና ደቡብ ክልሎች ያሉ አመራሮቹ እንደታሰሩበት እና የደረሱበት እንዳልታወቀ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ፓርቲው በአማራ ክልል በዋግኽምራ ዞን በሰቆጣ፣ በአዊ ዞን በቲሊሊ እና በምሥራቅ ጎጃም ዞን በሞጣ ከተሞች ሁለት አመራሮቹ የት እንደገቡ አለማወቁን እና አንድ አመራሩ ግን መታሰራቸውን ገልጧል።

በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ደሞ አንድ አመራሩ ከሥራ ቦታቸው ታፍነው መወሰዳቸውን የጠቀሰው ፓርቲው፣ አመራሮቼ ያሉበትን ሁኔታ ከምርጫ ቦርድ እና ከኢሰማኮ ጋር በመሆን እከታተላለሁ ብሏል።

LEAVE A REPLY