ኢሰመኮ ያለአግባብ የታሰሩት ሁሉም የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች እንዲፈቱ አሳሰበ

ኢሰመኮ ያለአግባብ የታሰሩት ሁሉም የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች እንዲፈቱ አሳሰበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በእስር ላይ የሚገኙ ሁሉም የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች እንዲፈቱ አሳሰበ።

ኮሚሽኑ ዛሬ እንዳስታወቀው፤ በትላንትናው እለት በፀጥታ ኃይሎች የተወሰዱትን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስን ጨምሮ 16 የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች እስካሁን ለእስር ተዳርገዋል።

ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ለረጅም ጊዜ መታሰር፣ የሚገኙበትን ቦታ ይፋ አለማድረግ እና ለእስር ባልተዘጋጁ ኢ መደበኛ ቦታዎች ማሰርና የሚድይ ደንቦችን መጣስ ችግሩን እያባባሰው መሆኑን ኢሰመኮ አስታውቋል።

ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ዶ/ርእንዳስታወቁት ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የታሰሩት የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች በሙሉ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

LEAVE A REPLY