እንቁ ጣጣሽ – ምን አመጣሽ ?! || አሥራደው (ከፈረንሳይ)

እንቁ ጣጣሽ – ምን አመጣሽ ?! || አሥራደው (ከፈረንሳይ)

  • ዞረሽ ዞረሽ ! ተሽከርክረሽ ተሽኮርምመሽ፤
    ተሽቀርቅረሽ ! ተሞናሙነሽተኳኩለሽ፤
    ቀናት ቆጥረሽ_ ወራት አዝለሽ ዓመት ሞልተሽ፤
    እኛን እረስተሽ_ ካለው ውለሽ ካለው ቀብጠሽ፤
    እንዳልነበርንእንደሌለን
    አፈር ትቢያ ጭቃ ለብሰን፤
    ምናምንቴ ከንቱ ሆነን፤
    ውልብ ላንል በትውስታሽ፤
    ከምናብሽ_ ከመዝገብሽእኛን ፍቀሽ፤
    እነ አባባ እነ እማማን፤
    ወንድም ጋሼ እ’ት ዓለምን፤
    ዘመድ አዝማድጎረቤቱን፤
    ሁሉን ትተሽ ሁሉን ረስተሽ፤
    ቀን አስልተሽ ወራት ቆጥረሽ ፤
    ዓመት ሞልተሽ ዘመን አዝለሽ፤
    እንቁጣጣሽ ምን አመጣሽ ? ለምን መጣሽ ?!
    ምን ትሠሪ ? ምን ትፈጥሪ ?
    ምን ታወሪ ? ምን ትነግሪ ?
    እኮ ለምን ?! ተናገሪ !!
    ለወገኔ ለተራበውበደል ጥቃት ላባዘነው፤
    ኑሮ ጨሶ ለሚያጨሰውበ’ንባዎቹ ለሚያጠቅሰው፤
    ጠኔ ጥሎት ለወደቀውበጎዳና ለሚተኛው
    ለእኔ ብጤ_ ለሷ ብጤ _ ለኛ ብጤው፤
    እንቁጣጣሽምን አመጣሽ ?!
    ተጠየቂ እስቲ እንስማሽ !!
  • መሬት ነጥቀሽ አርሶ አደሩን፤
    ሥራ ነፍገሽ ላብ አደሩን፤
    ለነጥቆ አደር ወለል አርገሽ _ በር ከፍተሽ፤
    ለዘራፊ፤ ለነጣቂ፤ ለሙሰኞች _ አዠርግደሽ፤
    ብዙሃኑን አስጨንቀሽበኑሮ ጣር አጎሳቁለሽ፤
    አንገላተሽ ገለሽ ቀብረሽ፤
    ከደላው ጋር እያሽቃበጥሽ፤
    ቀን አስልተሽ ወራት ቆጥረሽ፤
    ዓመት ሞልተሽ ዘመን አዝለሽ፤
    እንቁጣጣሽ ለምን መጣሽ ?! ምን አመጣሽ ?
    ተናገሪ እሲቲ እንስማሽ ?!
    ምን ትሠሪ ? ምን ታወሪ ?
    ምን ትፈጥሪ ምን ትነግሪ ?
    እኮ ለምን ?! ተናገሪ !!
    አንድ ቀን !!
    ኑሮን ሳይኖሯት፤ በቀዳዳ ብቻ እያጮለቁ፤ ለብዙ ዓመታት ሲመለከቷት ለቆዩት፤ ጎስቋሎች
    ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ መታሰቢያ ትሁንልኝ

LEAVE A REPLY