አቶ ግርማ የሺጥላ ተገደሉ

አቶ ግርማ የሺጥላ ተገደሉ

የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል።

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ” ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል። ” ብለዋል።

ዶ/ር ዐቢይ የግድያውን ሁኔታ በተመለከተ ዝርዝር_መረጃ ባይሰጡም ” ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባህል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳብ የተለየንን ሁሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሣት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው ” ሲሉ ገልጸውታል።

” ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ፣ ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች የፈጸሙት አስነዋሪና አሰቃቂ ተግባር፣ ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው። ” ሲሉ አክለዋል።

የብአዴኑ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ሃላፊ ግርማ የሺጥላ በጥይት ተደብድቦ መሃል ሜዳ ሆስፒታል ቢገባም በህይወት ሳይተርፍ መቅረቱን ተረጋገጠ።

ጉዳቱ የደረሰው በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ መሃል ሜዳ ከተማ ስብሰባ አድርገው በመመለስ ላይ ባሉበት ወቅት መሆኑንም ታውቋል።

ግርማ የሺጥላ በህይወት ስለመትረፉ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም ብለው የነበሩት ምንጮቹ የዞኑ አስተዳዳሪን ጨምሮ አብረውት የነበሩት በሙሉ በህይወት ስለመትረፋቸውም በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም ብለዋል።

ጓሳ በምትባለው አካባቢ ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት በተፈጸመው በዚህ ጥቃት በህይወት ላይተርፍ ይችላል የተባለውን ግርማ የሺጥላን ወደ ሌላ ሆስፒታል ለማዛወር ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም በህይወት ግን ሊተርፍ አለመቻሉን ገልጸዋል።
እስካሁን ግርማ የሺጥላ የተገደለው ከየትኛው ወገን በተፈጸመ ጥቃት መሆኑን ማወቅ እንዳልተቻለም ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY