አብዛኛዎቹ የአማራ የትግራይና የአፋር ከተሞች ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቆርጠ

አብዛኛዎቹ የአማራ የትግራይና የአፋር ከተሞች ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቆርጠ

ባህር ዳር – በደብረታቦር – ንፋስ መውጫ – ጋሸና – አላማጣ አብዛኞቹ የአማራ  ክልል ከተሞች   እንዲሁም የአፋር ክልል ዋና ከተማ  ሰመራና የተለያዩ የአፋር የክልል ዞኖችና ወረዳዎችን ጨምሮ የትግራይ ክልል ዋና ከተማን መቀሌ አብዛኛዎቹ  የአማራና የትግራይ ክልል ከተሞች  ከዛሬ ረፋድ ጀምሮ የኤሌትሪክ ኃይል እንደተቋረጠ  በጨለማ መዋጣቸውን ነዋሪዎች ገለፁ።  

ባህር ዳር – በደብረታቦር – ንፋስ መውጫ – ጋሸና – አላማጣ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት በመበጠሱ የአፋር ክልል ዋና ከተማ  ሰመራና የተለያዩ የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች እንዲሁም  የትግራይ ክልል ዋና ከተሞች መቀሌን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ከተሞች የኤሌትሪክ ኃይል እንደተቋረጠ ተሰምቷል።

ይህ በንዲህ እንዳለ  ከትላንት በስቲያ እሁድ የካቲት 24 ቀን2016 ጀምሮ ከደብረ ብርሃን – ሸዋሮቢት – ኮምቦልቻ የተዘረጋው መስመር በሸዋ ሮቢት ከተማ አቅራቢያ በመበጠሱ ከሸዋ ሮቢት እና ከሚሴ ከተሞች በስተቀር አብዛኛዎቹ የሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች  ከኮምቦልቻ በባቲ ኃይል ሲያገኙ የነበሩት ሠመራ እና የተለያዩ የአፋር ክልል ዞኖች እና ወረዳዎች እንዲሁም በወልድያ አላማጣ መስመር ኃይል ሲያገኙ የነበሩት መቀሌን ጨምሮ አብዛኛዎቹ የትግራይ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል እንደተቋረጠባቸው ጨለማ ውስጥ መዋልና ለማደር መገደዳቸውን  ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

LEAVE A REPLY