በሶማሊያ አዲስ ህገመንግስት ለማርቀቅ ምክክር ተጀመረ

በሶማሊያ አዲስ ህገመንግስት ለማርቀቅ ምክክር ተጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሶማሊያ ፌዴራላዊት መንግስት የሀገሪቱ አዲሱ ህገ መንግስት ለማርቀቅ ሁሉን አቀፍ ምክክር ቅዳሜ እለት ከሶማሊያ የፌደራል አስተዳደር ስር ካሉ ክልሎች አንዷ በሆነችው በፑንትላንድ ዋና ከተማ ጋሮዌ ከተማ ተካሄደ።

በምክክሩ ላይ የቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዚዳንቶች ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ እና ሻሪፍ ሼክ አህመድ ፣ ሀገሪቱ አዲሱን ህገ-መንግስቷን እንዴት እንደሚረቀቅ በትካሄደ ስነስርአት ላይ በአንድነት ታድመዋል።

ሁለቱ የቀድሞ መሪዎች በተጨማሪ የፑንትላንድ ፕሬዝዳንት ሳይድ አብዱላሂ ዴኒ ከሌሎች ፖለቲከኞች ጋር በሞቃዲሾ የፓርላማ የህግ አውጭ አካላትን ጨምሮ የተሳተፉበት ውይይት አድርገዋል። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY