በጋምቤላ በአውቶቢስ ላይ ጥቃት ተሰነዘረ – በአደጋ ሰዎች ሞተዋል

በጋምቤላ በአውቶቢስ ላይ ጥቃት ተሰነዘረ – በአደጋ ሰዎች ሞተዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ረቡዕ ማርች 27 ቀን 2024 ዓ.ም ረፋዱ ላይ ከጋምቤላ ከተማ ወደ ጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን ላሬ ወረዳ ሲጓዝ ላይ በነበረ አውቶብስ ላይ የታጠቁ ኃይሎች በሰነዘሩት የደፈጣ ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ቆስለዋል።

ምንጮች ከስፉራው እንደአሳወቁት ጥቃቱ የተፈፀመው በአቦል አውራጃ እና በታራፓም የስደተኞች ካምፕ መካከል ከቀኑ 10 ሰአት ላይ አውቶብሱ በጉዞ ላይ እያለ ነው። ዛሬ ማለዳ ላይ አውቶቡሶች በኮንቮይ ታጅበው ከጋምቤላ ከተማ መውጣታቸውን  ጥቃቱ የተሰነዘረበት   አውቶብስ በጉዞው በመዘግየቱ ለታጣቂዎች  ድንግተኛ ጥቃት እንዲጋለጥ አድርጎታል ተብሏል።

በሟቾቹ ላይ አንዲት ሴት፣ ህፃን እና የአውቶብስ ሹፌር ሲሆኑ  በጥይት ተመተው መሞታቸውን በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት የት እንዳሉ የማይታወቁ ተሳፋሪዎች አሉ። ብለዋል ስለጉዳዩ የተናገሩ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የጋምቤላ ነዋሪ 

ይህ በእንዲህ እንዳለ በትላንትናው እለት ማርች 26 ቀን 2024ከ ጋምቤላ ከተማ በ50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው አቦቦ ወረዳ 5 ሰዎች መሞታቸውም ምንጮቹ ገልጸዋል።  (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY