ንግድ ባንክ  14441 ግለሰቦች ገንዘቤን መልሰዋል አለ

ንግድ ባንክ  14441 ግለሰቦች ገንዘቤን መልሰዋል አለ

  • 565ቱ እስከ ቅዳሜ መልሱልኝ እያለነው!!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በሂሳብችሁ ከተቀመጠ ገንዘብ ውጭ  በሕገወጥ መንገድ ገንዘብ የወሰዱ ግለሰቦች ገንዘቡን እስከ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ተመላሽ እንዲያደርጉ በአሳሰበው መስረት።

14441 የሚሆኑ ግለሰቦች በተሰጠው ጊዜ ገደብ ተጠቅመው የወሰዱትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ እና በከፊል መመለሳቸውን  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባወጣው መግለጫ 565 ግለሰቦች ባንኩ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም  ያለአግባብ  የወሰዱትን ገንዘብ ባለመመለሳቸው ባንኩ ቀደም ሲል ባስጠነቀቀው መሠረት የስም ዝርዝራቸውን  በመኃበራዊ ሚዲያዎች ይፋ እንዲሆን አድርጎል።

እስከ ቅዳሜ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ገንዘቡን ያልመለሱ ካሉ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎችን በመጠቀም ሙሉ ስማቸውን፣ ፎቶዋቸውን፣ በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ በመውሰድ ወንጀል መጠርጠራቸውን በመጥቀስ ለሚመለከታቸው የሕግ አካላትና ተቋማት በማሳወቅ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY