አሜሪካ በአማራ ክልል ሰላማዊ ሰዎች መገደልና መፈናቀል ጉዳት አሳሰባኛል አለች

አሜሪካ በአማራ ክልል ሰላማዊ ሰዎች መገደልና መፈናቀል ጉዳት አሳሰባኛል አለች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞን በተፈጸሙ ጥቃቶች፤ ሲቪሎች መገደላቸው፣ ጉዳት መደረሱ እና የሰዎች መፈናቃል እንዳሳሰባት ገልፀዋል።

ኤርቪን ማሲንጋ፤ ዛሬ መጋቢት 17 ቀን 2016 ባስተላለፉት መልዕክት  “የትኛውም የግጭት ተዋናይ ሁከትን በመጠቀም ሰዎችን ከቤታቸው ማፈናቀል የለበትም”  ሲሉ አሳስበዋል። 

አገራቸው አሜሪካ፤ የኢትዮጵያ ውስብስብ የፖለቲካ እና የፀጥታ ቀውሶችን ለመፍታት የሲቪሎችን ጥበቃ እና የውይይት ቁርጠኝነት እንዲኖር ጥሪ ማቅረቧን አስታውሰዋል።  (EN – ኢትዮጵያ ዛሬ)

LEAVE A REPLY