የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ተገለፀ

የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ተገለፀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚወስደው መንገድ በመዘጋቱ  የደሴና አካባቢው ነዋሪዎች ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን የደሴ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።  

አስተዳደሩ  ለከተማው ህዝብ ፍጆታ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማከፋፈል ከአዲስ አበባ የተገዛ 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሊትር ዘይት፣ 1 ሺህ 400 ኩንታል ስኳር እና ሌሎች የኢንዱስትሪ ምርቶችን  ወደ ከተማው ማጎጎዝ ባለመቻሉ የከተማው ነዋሪ ለኑሮ ውድነት ለከፍተኛ እንግልት ተዳርጓል ብለዋል የከተማው አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች።

የደሴ ከተማ ነዋሪዎች መንግስት ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚወስደውን አውራጎዳና ላልተወሰነ ጊዜ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዳይሰጥ በማድርግ በሰላማዊ ን ህዝብ እየጎዳ ነው።

ይህንን መሰሉ እርምጃ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ሌላው ይቅር በእጀባ እንኳን የተገዛውን ለህብረተሰቡ የእለት ተዕለት ኑሮው የሚያስፈልገውን የፍጆታ ግብአት ሊያቀርብ  ይገባል ብለዋል አስተያየት የሰጡ የከተማው ነዋሪዎች። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY