አየር መንገድ 49 ጉምሩክ  ሰራተኞች ላይ እርምጃ ወሰደ  

አየር መንገድ 49 ጉምሩክ  ሰራተኞች ላይ እርምጃ ወሰደ  

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በስምንት ወራት ውስጥ  በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተመደብው ሲሰሩ የነበሩ 49 የጉምሩክ ሰራተኞች እና ከፍተኛ አመራሮች  ላይ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ ተወስዷባቸዋል ተባለ። 

የጉምሩክ ኮሚሽን በሰራተኞቹ ላይ የሚቀርቡትን ቅሬታዎች ለመቅረፍ “ረጅም ጊዜ” የወሰደ ጥናት መካሄዱ  የኮሚሽኑ ዳይሬክተር መናገራቸው ታውቋል። 

በጥናቱ መሰረት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የሚሰሩ የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞን ለመቀየር፣ ለማሸጋሸግ እና በድጋሚ ለማዋቀር ዝግጅት ተደርጓል ማለታቸውም ተሰምቷል። 

እርምጃው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅሬታዎቹ ላይ ምርመራ መጀመሩን ማስታወቁን ተክትሎ ይሁን ቀደም ብሎ በተጠና ጥናት ስለመሆኑ ኮምሺነሩ አልገለፁም። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY