የአቶ በረከት እና ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) የፍርድ ቤት ውሎ እያወያየ ነው

የአቶ በረከት እና ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) የፍርድ ቤት ውሎ እያወያየ ነው

/ኢትዮጵያነገዜና/፡- በባህርዳር ፍርድ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ የታየላቸው አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሣ ያቀረቡት ጥያቄ መወያያ ሆኗል።

የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ በዛሬው ቀጠሮ በተከሳሾቹ ላይ የቀረበው ክስ ውስብስብና ድንበር ተሻጋሪ ከመሆኑም በላይ ምስክሮች እና ሰነዶች በሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ መገኘታቸውን ጠቅሶ  ለምርመራ ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው በድጋሚ ጠይቋል።

የመክሰስ ሥልጣን  የሌለው አካል እንደተከሱ በመጥቀስ የጊዜ ቀጠሮውን የተቃወሙት አቶ በረከት ሰምኦን ሲሆኑ ሰነዶች ተሟልተው እንደሚገኙና ሳያጣራ መታሰራቸውን በመጠቆም የጊዜ ቀጠሮውን እኛን በእስር ለማቆየት የታሰበ መሆኑን አቶ ታደሰ ካሣ ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት የጊዜ ቀጠሮውን ተቃውመዋል።

አቶ በረከት ስንገባም ስንወጣም መልካም  ስማችንን የሚያጎድፍ ስድብ እየተሰደቡ መሆኑን በመግለጽ አቤቱታ ከማቅረባቸውም በላይ ጠበቃ ማግኘት ባለመቻላቸው መንግስት እንዲያቆምላቸው ጠይቀዋል።  በተጨማሪም የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውን ጠቁመው ኮምፒዩተር እንዲገባላቸው ጥያቄ አቅርበዋል።

የከሳሽ ተከሳሽን ቃል ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ መረጃዎች በተለያዩ ሃገራት መገኘታቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት አቃቤ ሕግ የጠየቀውን የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል።

የተከሳሾችን የፍርድ ቤት ውሎ በሚመለከት አስተያየታቸውን የገለጹ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ለኢትዮጵያ ነገ ድረገጽ እንደገለጹት ከዚህ በፊት እነአቶ በረከት እንደፈለጉ ያዙበትና ውሳኔያቸውን በብጣሽ ወረቀት በመላክ ፍርድ በሚሰጡበት የፍትህ ስርአት እንደነበር አስታውሰው በኢትዮጵያ የፍትህ ስርአት መገንባት  በሚደረገው ጀምሮ በእነ አቶ በረከት ላይ ሊተገበር እንደሚገባ አመልክተዋል።

አስተያየት ሰጪው ተከሳሾቹ ከዚህ በፊት በጋዜጠኞች፣  በፖለቲካ አመራሮች፣ በሰብአዊ ተሟጋቾች ብቻ ሳይሆን የእለት ኑሮአቸውን ለመግፋት በሚፍጨረጨሩ ንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሱት ግፍ በታሪክ የማይረሳ መሆኑን በማከል የጠየቁት የኢንተርኔትና የኮምፒውተር ጥያቄ እንደስላቅ ያዩት መሆኑን ጠቅሰው እንደ አንድ ታራሚ በአግባቡ መያዝ እና ለማናቸውም አገዛዝ መማሪያ መሆን እንዳለባቸው እንደሚያምኑ ገልፀዋል።

የክሱን ሂደት በሚመለከት በርካቶች አስተያየት የሰጡ ሲሆን የሚገባቸውን አግኝተዋል የሚሉ ሰዎች ክሱ በሰብአዊ መብትና እስከ ዘር ማጥፋት ሊዘልቅ ይገባል ከሚሉ እስከ በጠባብ ክፍል መታሰራቸውን ማየት ብቻ በቂ ነው እስከሚሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አንዳንዶቹ አቶ በረከት በእስረኞች እና በአስረኛ ቤተሰቦች ላይ እንዴት ይሳሏለቁ እንደነበር በማስታወስ መርካታቸውን ገለጸዋል።

የአቶ በረከት ልጆች ከባህር ዳር አዲስአበባ መመላለስ እንዳሳዘናቸው የገለጹ አስተያየት ሰጪዎችም ተከሳሾቹ በልጆቻቸው ፊት መሰደባቸው አግባብ አይደለም ሲሉ እናትን በልጅ አስክሬን ላይ በማስቀመጥና በህጻናት ሞት የሚጠየቅ ዘግናኝ አገዛዝ ፈላጭ ቆራጭ ሰው የሚደረግለት አያያዝ ከበቂ በላይ ነው በማለት ቁጣቸውን አሰምተዋል።

LEAVE A REPLY