የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ “ሕወሓት” እና “ሸኔ” የሽብርተኝነት ረቂቅ ላይ...

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ “ሕወሓት” እና “ሸኔ” የሽብርተኝነት ረቂቅ ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሄደው 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ስብሰባ “ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል፡፡

በአሁኑ ሰአት በሽብርተኝነት እንደታዩ የሚኒስትሮች ምከር ቤት ውሳኔ ያሳለፈባቸው ሕወሀት እንደ ድርጅትም ሆነ በመዋቀር የሚሰራ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ሸኔ ተብሎ የተጠቀሰው ቡድን ግን ስለመኖሩ  መንግሰት ከሚገለጸው ተደጋጋሚ ክስ በስተቀር እኔ ሸኔ ነኝ በሎ የቀረበ አካል አለመኖሩ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል።

ገዥው መንግሥት ባለፉት ዓመታት ኦነግ ሸኔ እያለ ይጠራው የነበረውን ቡድን ሸኔ በሚል በሽብርተኝነት መፈረጁ ጥያቄዎችን አጭሯል።

ከዚህ በፊት በሸኔነት የተፈረጀው ጃልመሮ የተባለ የሸማቂ መሪ ሼኔን አላውቅም እኛ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ተብለን  ነው የምንጠራው ማለቱ የታወሳል።

LEAVE A REPLY