አዲስ አበባ ተቆላልፋለች፤ ፖሊስ እና ሠራዊቱ በህዝብ ላይ አልተኩስም ብለዋል (ክንፉ አሰፋ-አምስተርዳም)

አዲስ አበባ ተቆላልፋለች፤ ፖሊስ እና ሠራዊቱ በህዝብ ላይ አልተኩስም ብለዋል (ክንፉ አሰፋ-አምስተርዳም)

በሳምንቱ መግቢያ የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ ብሔራዊ እርቅ እና ድርድር እንዲደረግ ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል። አምስቱ የህወሓት ቁንጮዎች ትዕቢት የተሞላበት ምላሽ ነው የሰጡት። ከድርድር ይልቅ ከህዝብ ጋር ጦርነት መግጠምን መርጠዋል።

አብዛኛው የፖሊስ እና የህገር መከላከያ ሠራዊቱ “ህዝብ ላይ አልተኩስም” ማለታቸው የህወሓት አመራርን ጭንቅ ውስጥ አስገብተውታል።

አዲስ አበባ ተቆላልፋለች። በአራቱም አቅጣጫ በኩል የሚገባም የሚወጣም የለም። መንገዶች በሙሉ ተዘጋግተዋል። ስልክ እና ኢንተርኔት ጠፍቷል።

በአዲስ አበባ ዙርያ ባሉ ከተሞች ሰኞ መስከረም 23 ቀን የተጀመረውን ህዝባዊ አመጽ ለማዳፈን በህወሓት የተወሰደው የአፈሳ እርምጃ አመጹን አላቆመውም። ሰኞ ማምሻውን በሺዎች የሚቆጠሩ ዘጎች ታፍሰው ወዳልታወቀ ስፍራ በወሰዳቸው ሳብያ አመጹ በዛሬው እለት ተባብሶ ቀጥሏል። የአካባቢ ፖሊሶችም ከህዝብ ጋር በመሆን በአመመጹ እየተሳተፉ በመሆኑ የስራአቱን ቁንጮዎች ጭንቀት ውስጥ ከቷቸዋል።

ሰበታ ላይ የነበረው የቱርክ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ እና የኬብል ፋብሪካ በትናንትናው ዕለት መውደሙን ሮይተርስ ከስፍራው ዘግቧል። በሆለታ በነበረው አመጽ ሚስ ሻሮን ሬይ የተባለች አሜሪካዊ የግብርና ኤክፐርት መገደልዋንም ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቦ ነበር። ይህ ዜና በዓለም የመገናኛ ብዙኃን ከተሰማ በኋላ ህወሓት የስልክ እና የኢንተርነት አገልሎት እንዲቋረጥ አድርጓል። የአመጹ ዜና ወደ ሌሎች እንዳይሰራጭ ታቅዶ የተደረገው ይህ ድርጊታቸው የህዝብን ቁጣ እያበረታው መጥቶ ካድሬዎችን እየለቀሙ መምታት እንዲጀመር አስተዋጽኦ አድርጓል።

ህዝብ በጋራ ተነስቶ የህወሓት ተላላኪዎችን እያስጠነቀቀ ሲሆን እንቢ ያሉት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገናል። የወንጂ ስኳር ፍብሪካ ከፉተኛ ቃጠሎ የደረሰበት ሲሆን፣ ኤልፎራ የሼክ አል-አሙዲን የከብት ማደለቢያ ንብረት ሙሉ በሙሉ ወድሟል። በቀርሳ ወረዳ አንድ የህወሓት ተላላኪ በህዝብ ተገድሏል፣ በሆሮ ጉድሩ እና በጉጂም የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ላይ ህዝብ እርምጃ ወስዶባቸዋል። በድሬ ዳዋ ዲፖ ጋዝ ስቴሽን ቤሳት ጋይቷል።

የናይጄሪያዊው ኪሎ ዲንጎቴ ንብረት የነበረው ዲንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ በህዝባዊ አመጽ መውደሙን የአፍሪካ ሜድያ ኔትወርክ ዘግቧል። ጉጂ ዞን ያለው የሼክ አላሙዲን የወርቅ ማእድን በትላንትናው እለት መውደሙን ማኅበራዊ ድረ-ገጾች ዘግበዋል።
ባዶ እጁን እየወጣ ሲገደል የነበረው የኦሮሞ ህዝብ አሁን ራሱን ራሱን የሚከላከልበት መሳርያ እየያዘ መውጣቱን የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ። በአለም ገና ዳሽን ባንክ እና ከገዥው ፓርቲ ጋር ንክኪ ያላቸው መኪናዎች ተቃጥለዋል።

በአርሲ፣ በመቱ እና በጂማ በተማሪዎች የተቀሰቀሰው አመጽ እንደቀጠለ ነው። የጅማ ወህኒ ቤት ተቃጥሎ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ እንዲፈቱ የተደረገው ትላንት ምሽት ላይ ነበር።

አዲስ አበባ ከእሬቻው እልቂት በኋላ የሙት ከተማ መስላለች። የንግድ እንቀስቃሴ በሙሉ ቆሟል። ሱቆች ዝግ ናቸው፣ የህዝብ ትራንስፖርትም የለም። መርካቶም ጸጥ-ረጭ እንዳለች ነው። በዛሬው እለት ታክሲ በከተማዋ ባለመኖሩ አብዛኛው ሰው ስራ አልገባም። ከተወሰኑ የግል ትምህርት ቤቶች በስተቀር የመንግስት ትምህርት ቤቶች አሁንም ዝግ ሆነው እንዲቆዩ ተወስኗል። አንዳንድ የግል ት/ቤቶች ወላጆችንን ልጆቻቸውን ወደ ት/ቤት እንዳይልኩ እየመከሩ ይገኛሉ።

ለአዲስ ተማሪዎች ጥሪ ያደረገው የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ብቻ ነው። ሌላዎቹ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ተማሪ ገብቶ የመማሩ ጉዳይ የሚታሰብ አይደለም።

በደቡብ ወደ ሻሸመኔ እና ወደ አዋሳ የሚወስደው መንገድ እሁድ ጀምሮ ዝግ ነው። በሰሜን ሱልልታ፣ ለገዳዲ፣ ቦሌ ቡልቡላ፤ በም እራብ በአስኮ፣ በቡራዩ፣ ሰበታ፣ አለምገና፣ ብስራተ-ገብሬል፣ አየር ጤና፣ ወልሶ፣ ወደ ሆሳዕና እና ጅማ የሚወስዱ መንገዶች በሙሉ ተዘግተዋል። በዚያ የሚተላለፍ ተሽከርካሪ ቢገኝ የድንጋይ ናዳ ይወርድበታል።

አጋዚ ይህ ህዝባዊ አመጽ ከቁጥጥር ውጪ ስለሆነበት አዲስ አበባን ብቻ ከብቦ እየጠበቀ፣ ንጹሃን ዜጋን በማፈስ ስራ ላይ ተጠምዷል።

ህወሓት በአማራው ህዝብ ላይ በይፋ ያወጀው ጦርነት አልተሳካም። ራሱን ከመከላከል አልፎ አካባቢውን ከአጋዚ ነጻ እይደረገ ይገኛል። በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ከእስር ነጻ ወጥተዋል። የባህርዳር ዩንቨርስቲ እስካሁን እንደተከበበ ነው። የኮሶበር ህዝብ የዳሽን ቢራን ጭኖ የነበረ ከባድ መኪና ከአገልግሎት ውጪ ሆኗል።

በባህር ዳር ወጣቶችን ሲያሰቃይ የነበረ የማንኩሳ ተወላጅ ማንነቱ ባልታወቀ አካል ተገድሎ መገኘቱ በማኅበራዊ ድረ-ገጽ ተዘግቧል።

የህወሓት ባለሥልጣናት አሸንዳን በርችት፣ እሬቻን በጥይት ካስተናገዱ በኋላ በወገን ላይ በደረሰው አሰቃቂ እልቂት መላው የአኢትይኦጵያ ህዝብ ብሔራዊ ሃዘን ላይ ነበር።

ብሔራዊ ኀዘን ላይ የነበረው ህዝብ ወደ ብሔራዊ አመጽ የገባ ይመስላል። ሰላማዊ ህዝብን እንደ ግራዚያኒ፣ እንደ ሞሶሎኒ በጥይት እና በመርዝ ጭስ ከጨረሱ በኋላ በቴሌቭዥን ወጥተው አዝነናል እያሉ፣ ቁስልን የባሰ ሲነካኩበት ከዚህ ውጭ አማራጭ የለም። ህወሓቶች ይልቁንም ለራሳቸው ይዘኑ። ሰላማዊውን ህዝብ እየጨረሱ ያሉት ሁሉ በተራቸው የሚያለቅሱበት ግዜ ሩቅ አይደለም። በደም የታጠበ እጃቸው ገና ሳታደርቅ በቴሌቭዥን ወጥተው በሟች አጽም ላይ መቀለዳቸው ሳያንስ በተለመደ የሽብርተኞች ዲስኩር ህዝብ ላይ እጅ መቀሰር ድፍረት ነው።

ግዜ ሊወስድ ይችል ይሆናል እንጂ እነዚህ ነብሰ-ገዳዮች የእያንዳንዱ ነብስ ዋጋ መክፈላቸው አይቀሬ ነው።

የቢሾፍቱው ግድያ የህወሓት “ጥልቅ ተሃድሶ” ጅማሬ መሆኑ ነው። ግን ህዝብን እየረገጡ ብዙ ሊዘልቁ አይችሉም። ፍም እሳት የሆነ የአመጽ ትውልድ ተፈጥሯል። እነሱ ባሰሩ እና በገደሉ ቁጥር ሚሊዮን ሆኖ የሚነሳ ትውልድ። ምንም ነገር ሳይዝ በድምጹ ብቻ የሚያስፈራ ትውልድ። ህዝብን ጠላት አድርጎ ለመግዛት የሚሞክር ሥርዓት ይህንን ሁሉ ህዝብ ከቶውንም ገድሎ ሊጨርስ አይችልም።

LEAVE A REPLY