ተመፃዳቂ መስማት አስመሳይ ማየት መረረን! | መስፍን ማሞ ተሰማ

ተመፃዳቂ መስማት አስመሳይ ማየት መረረን! | መስፍን ማሞ ተሰማ

ሠላም ለናንተ ይሁን!

እነሆ ለዘመናት እየተነሳ ሲወድቅ የኖረው የለውጥ ማዕበል መርከቡን ከነመልህቁ መሪውን ከነኮምፓሱ ካገኘ ዘጠኝ ወራት ተቆጠሩአብያዊው መንግሥት! ሲመተ አብይ ዓመት ሊሆነው ሶስት ወራት ብቻአጃኢብ ነው!

የስንትና ስንት ዓመታቱን ጉድ በዘጠኝ ወር አየን? በዘጠኝ ወር በሆድ ያደገ ቅሪት ሰው ሆኖ ይወለዳልየፈጣሪ ተዓምርእኛም በፈጣሪ ተዓምር በዘጠኝ ወራት ሩቅ ተጉዘናልሰው መሆን ጀምረናልሙሉዕ ለመሆን ግና ረዥምና ጥቅጥቅ ጥሻ ማለፍ እልፍ ደረጃዎችም መውጣት ይቀረናል

ከድቅድቁ የጨለማው ዘመን ገዢ ከህወሃት አገዛዝ ነፃ ወጥተናልበነፃነት መኖር ግን አልጀመርንምስጋታችን ብዙ ሠላማችንም ስስ ነውና የጨለማው ዘመን አጋፋሪዎች ወር አልፎ ወር ሲተካ ምሽጋቸውን እያጠናከሩና አይነኬ እየመሰሉ መጥተዋልየጥፋት ድርጊቶቻቸውን መዘርዘር ደግሞ ታክቶናል ፍትህን ስንቀርበው እየራቀን ይመስላል

የህወሃቱ የመቀሌው መንግሥት ከአብያዊው መንግሥት ጋር የአይጥና ድመት ጨዋታውን አድርቶታል። ዶ/ር ደብረፅዮንኢህአዴግ <ድብብቆሽ> ላይ ነው ይለናልትግራይ ለማዕከላዊው መንግሥት እንደማትታዘዝ ደጋግሞነግሮናልምፀት ነው መመፃደቅ? በዚያኛው ሰፈር ደግሞ አዲስ አበባ ላይሁሉ የኦሮምያ ህዝብ ከነፈረሱ ወጥቶ የተቀበለው ኦነግ ወለጋና ቦረና መሽጎ ይፋዊ ጦርነት ከፍቷልመሪዎቹም አዲስ አበባ ላይ እየፏለሉ አብያዊውን መንግሥት እንደራደር ይሉታልምን ይሉት መመፃደቅ ነው? ጎፈሬያም ጦረኞቻቸው ግን ሀገርና ህዝብ ያሸብራሉ ባንክ ይዘርፋሉነውረኛ ድርጊት በህዝብ ላይ ይፈፅማሉስማቸው ግን ነፃ አውጪ ነው!! ተፅዕኖ ፈጣሪ ቦታ የያዙ አስመሳይ የለውጥ ደጋፊ ኦነጋውያን በርካቶች ይመስላሉ

ደግሞ በዚያ ሰሞን ዶ/ር አብይና ዶ/ር ደብረፅዮን የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ሲከፈት እጅ ለእጅ ተቆላልፈው ሲታዩ ተጠፋፍተው የተገናኙ ወንድማማቾች ይመስሉ ነበርየዶ/ር አብይን እጅ ጨብጦ የያዘው የህወሃቱ መሪ ግን ሽሬ ላይ መከላከያ ከነመሳሪያው እንዳይንቀሳቀስ ሠላማዊ ህዝብ አሰልፏልከህወሃት ዕውቅናና ይሁንታ ውጪ አንዳች በትግራይ ምድር አይደረግማና! በዛኑ ጊዜ ደግሞ በህወሃት የተደራጁ የትግራይ ተወላጆች ዶ/ር አብይንና አቶ ገዱን <ሌባሌባ> እያሉ ሳደቡ መተማ ላይ አይተናል ጥቂት ቀን አሳልፎ ደግሞ መከላከያን ያገቱት የሽሬ ወጣቶች<ተሳስተው> ነበር ብሎ የህወሃቱ መሪ መግለጫ ሰጥቷልምን ይሉት ማስመሰል እንደምንስ ያለ መመፃደቅ ነውየትግራይ ክልል ከፌዴራል ጋር ጡንቻውን የሚለካካ ይመስላልይህን የተደጋገመ ድራማ መመልከት ሰልችቶናል! ምርርም እያለን ነው!

ስለ ጌታቸው አሰፋና ስለግብረበላዎቹ የምንሰማው ሁሉ የሰለቸ ሙዚቃ እየሆነብን ነውየለውጡ ዕድሜ ሲገፋ <ኮትገልባጩ> አስመሳዩ በመበራከቱ በሲቪሉና በወታደሩበየመስሪያ ቤቱና ማህበራዊ ህይወቱበሃይማኖቱና በፖለቲካበሥነ ጥበብና በሙዚቃው ማንን ከማን ለመለየት እየቸገረ ነው ከለውጡ ማዕበል ጋር ነበርኩበት አለሁበትም ባዩ በዝቷል

በይቅርታው ጣራ በደቡብ ኢትዮጵያ የዘመነ ህወሃት ቆመጥ ነበሩት ሳይቀሩ አምባሳደርነት ተሹመዋልእኛም ጉድ ብለናል። ለውጡ በአስመሳዮችና ተመፃዳቂዎች እንዳይወረር ያሰጋልአስመሳዩ እስኪጠራተመፃዳቂው እስኪገታ ስንት ጊዜ ፈጅ ይሆን?!

ኢህአዴግን ታግለን ኢህአዴግን ደግፈናልና አሁን ኢዮባዊ ትዕግሥት ያስፈልገናልአብያዊውን መንግሥት በንቃትና በምክንያት መደገፍና ማራመድ!! በዛም ሆነ በዚህ ግን ኢትዮጵያ ከገባችበት የታሪክ አጣብቂኝ ለመውጣትና ሲነጋ ለማየት ከአብያዊው መንግሥት ውጪ በዚህ ኢትዮጵያ ከቶም ሌላ ምርጫ የላትም!! ትዕግስትና ፅናቱን ይስጠን እንጂ!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይታደግ!

ጥር 2011 ዓ/ም (ጃንዋሪ 2019)

ሲድኒ አውስትራሊያ

mmtessema@gmail.com

LEAVE A REPLY