አሜሪካና ካናዳ ቦይንግ 737 8 ማክስ እንዳይንቀሳቀሰ አዘዙ | ኢትዮጰያ ሁለት የቱርክ...

አሜሪካና ካናዳ ቦይንግ 737 8 ማክስ እንዳይንቀሳቀሰ አዘዙ | ኢትዮጰያ ሁለት የቱርክ 737 Max 8 እንዳያርፉ ከለከለች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና 157 ተሳፋሪዎችን በማጓጓዝ ላይ በድንገት የተከሰከሰወና የአለምን ተኩረት የሳበው የኢትዮጰያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302 ቦይንግ ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋን ተከትሎ ከአርባ በላይ ሀገራት አውሮፐላኑ አገለግሎት እንዳይሰጥ አዘዋል::

መዘግየታችውን ያመኑት ዶናልድ ትራምፕ ሚዛናዊ ማጣራት ከተደረግ በኋላ የአሜሪካዊያንንና የመላ ተጓዦችን ደህንነት ለመጥበቅ ሲባል ቦይንግ ማክስ 8 እና ቦይንግ ማክስ 9 አውሮፐላኖች አግርልግሎት እንዳይሰጡ ማድረጋችውን ተናግርዋል:: 18 ዜጎቿን በባለፈው እሁድ አሰቃቂ አደጋ ያጣችው ካናዳም ክልከላውን ተቀላቅላለች::

ኢትዮጰያም ሁለት የቦይንግ 737 አውሮፐላኖች በቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ እንዳያረፉ በመከልከል መመለሷን ይፋ አድርጋለች:: የተከሰከሰውን የአውሮፕላን አደጋ አስመልክታ የሀዘን ቀን ያወጅችው ኢትዮጰያ ጥቁር ሳጥን በመባል የሚታወቀውን የመረጃ ማከማቻ ለምርመራ ወደ ውጭ ሀገር እንደምትልክ ያስታወቀች ሲሆን በትክክል የት ሀገር ምርመራው እንደሚደረግ ለጊዘው ከምግለጽ ተቆጥባለች:: አሜሪካ መርመራው በሀገሯ እንዲደረግ የወተወተች ሲሆን የኢትዮጵያው አጣሪ ኮሚቴ ጥያቄውን ውድቅ እንዳደረገውእና ምርመራው በአውሮፓ እንደሚሆን መረጃዎች ያመለክታሉ::

LEAVE A REPLY