ትናንት ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው 19 ሰዎች በቤት ለቤት ምርመራ የተገኙ መሆናቸው ተነገረ

ትናንት ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው 19 ሰዎች በቤት ለቤት ምርመራ የተገኙ መሆናቸው ተነገረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ መረጃ (የሚቀበልበትን ነፃ የስልክ መስመር ይፋ አደረገ፡፡ የከተማዋ ነዋሪዎች በ6406 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ስለ ኮሮና ቫይረስ መረጃ መስጠት እና ማግኘት ይችላሉ ሲልም አስታውቋል፡፡

ነፃ የስልክ መስመሩ ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የጠቆመው የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ፤ እስካሁን የራሱ ነፃ የስልክ መስመር ያልነበረው ሲሆን፣ በሀገር ዐቀፍ መስመር በኩል ሲገለገል መቆየቱንም ገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተነገረው ሀያ አምስት ሰዎች መሀል አስራ ዘጠኙ ሰዎች በቤት ለቤት በተደረገ ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው መሆኑ ተነግሯል:: እነዚህ የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት ወጣቶች ምንም ዓይነት የውጭ ሀገር ጉዞ የሌላቸው መሆናቸውም ይታወቃል::

LEAVE A REPLY