አቶ በረከት 6 ዓመት አተ ታደሰ 8 ዓመት ተፈረደባቸው

አቶ በረከት 6 ዓመት አተ ታደሰ 8 ዓመት ተፈረደባቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሥራን በማያመች መንገድ መርተዋል በሚል  የሙስና ወንጀል የከሰሳቸው የቀድሞ ባለስልጣን አቶ በረከት ስምዖን እና ታደሰ ካሳ የፍርድ ውሳኔ ተሰጠ።

ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የክሱን ክርክር ሲመለከት ከቆየ በኋላ ነበር ሚያዝያ 26 ቀን 2012 ዓ.ም ጥፋተኛ መሆናቸውን ነው የገለፀው፡፡

ከትላንት ወዲያ በከሳሽ እና በተከሳሽ መካከል የቅጣት ውሳኔ አስተያየቶችን ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለሚያዚያ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት በ1ኛ ተከሳሽ ሆነው የቀረቡት አቶ በረከት ስምኦን የስድስት ዓመት እስራትና የ10,000 ብር የገንዘብ ቅጣት የተወሰነባቸው ሲሆን ፡፡

2ኛ ተከሳሽ የሆኑት አቶ ታደሰ ካሳ  የ15,000 ብር መቀጫ ጋር የ8 ዓመት የእስር ተፈርዶባቸዋል፡፡

አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሠ ካሣ በጥረት ኮርፖሬሽንን በቦርድ ሰብሳቢነትና በዋና ሥራ አስፈፃሚነት ሚናቸው ጋር በተያያዘ ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ጥር 2011 ዓ.ም በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቶ ፤ከቀናት በፊት በሁለቱ የቀድሞ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ መተላለፉ አይዘነጋም።

አቶ በረከት ስምዖን በመጥፎነቱ የሚታወቀው የመለስ አገዛዝ ቀኝ እጅ የነበሩና የኮሙኒኬሽን ጽህፍት ቤት ሀላፊ በነበረበት ወቅት በተለይ አፋኝ የሆኑ የፕሬስ ሕጎች እንዲወጡና ጋዜጠኞችን በማንገላታት፣  በማዋከብ፣  በማሰቃየትና በማሰደድ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው መሆኑ ይታወቃል።

አቶ በረከትን የተከሱበት ክስ ከጥፋታቸው በታች የሆነ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች በሰው ልጅ ላይ በደረሰ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰትና ዘር ተኮር እልቂት ሊጠየቁ የሚገባቸው ክፉ ሰው ናቸው ሲሉ ይከራከራሉ።

 

LEAVE A REPLY