ግብፅ የጦር ሄሊኮፕተሮቿን ዘመናዊ ለማድረግ ለአሜሪካ  የ2.3 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ ፈጸመች

ግብፅ የጦር ሄሊኮፕተሮቿን ዘመናዊ ለማድረግ ለአሜሪካ  የ2.3 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ ፈጸመች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ግብፅ ያሏትን የጦር ሄሊኮፕተሮች አሜሪካ እንድታድስላት በጠየቀችው መሠረት ሁለቱ ሀገራት ከስምምነት ላይ መድረሳቸው እየተነገረ ነው::

በስምምነቱ መሠረት አሜሪካ የግብፅን 43 ኤ.ኤች፣ 64-ኢ አፓቼ  የተሰኙትን ሄሊኮፕተሮችን እድሳት ከማድረግ ባሻገር የጦር ሄሌኮፕተሮቹን በአዳዲስ የቴክኖዎሎጂ ውጤቶችም ታዘምናለች። በአንፃሩ ለዚህ አገልግሎት ግብፅ ለአሜሪካ 2.3 ቢሊየን ዶላር የምትከፍል ሲሆን፣ ይህ ወታደራዊ ስምምነት ከመጭው ሀሙስ ጀምሮ ሥራ ላይ እንደሚውልም ታውቋል።

የአሜሪካ መከላከያ ደህንነት ትብብር ኤጀንሲ  ሥራውንበበላይነት ይመራዋል ተብሏል:: ይኸው ኤጀንሲ ስለ ስምምነቱ ለኮንግረሱ ማብራሪያ እንደሰጠ መረጃዎች ይጠቁማሉ:: ወታደራዊ ጉድዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ዲፌንስ ዴይሊ እንደዘገበው ከሆነ የግብፅን ተዋጊ ሄሊኮፕተሮች ለማደስ የቀርበለትን ይህን የቢሊየን ዶላሮች ስምምነት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሙሉ ለሙሉ ተቀብሎታል።

ግብፅ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይ ወታደራዊ ኃይሏን በማጠናከር ላይ ትገኛለች ፤ ሀገሪቱ ባለፈው ሳምንት ዘመናዊ ወታደራዊ ጀልባ መግዛቷን የተለያዮ ዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎች ታማኝ ምንጮቻቸውን በመጥቀስ ዘግበዋል።

LEAVE A REPLY