በአዲስ አበባ በተጣለ ቦንብ አምስት ሕጻናት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ

በአዲስ አበባ በተጣለ ቦንብ አምስት ሕጻናት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአዲስ አበባ ከተማ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው በተለምዶ 02፣ ወይም “ካፒቴን ደምሴ ሰፈር ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሕጻናት ወድቆ ያገኙት ቦንብ እጃቸው ላይ ፈንድቶ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በተጠቀሰው ሥፍራ ሕጻናት በሚጫወቱበት ሜዳላይ የተጣለው የእጅ ቦንብ በአንድ የ13 ዓመት ሕጻን ላይ ከፍተኛ፣ በአራቱ ላይ ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው የኣካል ጉዳት ማድረሱን የከተማው ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
63A84485-6E35-416C-BFDD-44F9C36921F2
ጉዳቱ የደረሰባቸው አምስቱ ሕጻናት ወድቆ ያገኙትን ቦንብ መጫወቻ መስሏቸው “እኔ ልወሰድ፣ እኔ ልውስድ” በማላት ሲጓተቱ ቦንቡ የ13 ዓመት ታዳጊ በሆነው ቻላቸው ተሾመ እጅ ላይ በመፈንዳቱ ጉዳቱ ሊደርስ ችሏል።

LEAVE A REPLY