ፖሊሶች በርካታ የህወሐት ሰላዮችንና ተጠርጣሪዎችን በጉቦ እየለቁ መሆኑ ተገለጸ 

ፖሊሶች በርካታ የህወሐት ሰላዮችንና ተጠርጣሪዎችን በጉቦ እየለቁ መሆኑ ተገለጸ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአዲሰ አበባ ፖሊስ ከህወሓት ጋር ከፍተኛ ቁርኝት እንዳላቸው በህበረተሰቡ ተጠቁመው የተያዙ ሰዎችን እሰከ 500 ሺህ ብር ጉቦ በመቀበል እየለቀቁ መሆኑን የኢትዮጵያ ነገ ምንጮች ገለጹ።

በማህበረሰቡ ተጠቁመው የተየዙ የሀወሀት አባላትና ደጋፊዎችን ገንዘብ (ጉቦ) በመቀበል እንደሚለቁ እና ሀብት አለቸው ያሏቸውን ንፁሀን ዜጎቸም ‘ተጠርጥረሀል’ በሚል እያሰሩ ገንዘብ እንደሚቀበሉ መረጃ ደርሶናል።

ከበታች ሹም እስከ ከፈተኛ ሀላፊነት የተቀመጡ የፖሊስ አባላት በተቀናጀ መልኩ የገንዘብ መቀባበያ ሰንሰለት በመዘርጋት በቅንጀት እንደሚሰሩ ለመረዳት ተችሏል።

በተለይ በአሁኑ ሰአት ለሀገር ሕልውና ከፈተኛ ርብርብ በሚደረግበትና የሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ኢትዮጵያውያን በህብረት በተነሱበት ወቅት የከተማው ፖሊሶች በእንዲህ አይነት ርካሽ ስራ ላይ መሳተፋቸው እንዳሳሰባቸው የገለፁት ምንጮች አንድ ግለሰብ በሕዝብ ጥቆማ ለአምስት ጊዜ ያህል ታስሮ በሙስና እንደተለቀቀ እና ‘እድሜ ለገንዘቤ ወጣሁ’ ሲል መስማታቸውን ገለጸዋል።

የታማኝ ፖሊሶችን ምግባር የሚያጠለሽ እና የሀገርን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥለውን ይህንን ተግባር ለፖሊስ ቢያሳውቁም ምንም አይነት ምላሽ እንዳላገኙ የሚገልፁት እነኚሁ ተቆርቋሪ ዜጎች ከ50 ሺህ ብር እስከ 500ሺህ ብር ጉቦ ከፍለው የወጡ ሰዎች በማቀባበል ስራ ላይ ተሰማርተው መመልከታቸውንም ለኢትዮጵያ ነገ ተናግረዋል።

የገዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት የኢትዮጵያ ነገ ደረ ገጽ ዝግጅት ክፍላችን ለአዲስ አበባ ፖሊስ ፈጣን እርምጃ እንዲወስድና ምላሹን እንደሰጥ የጠየቅን ሲሆን ምላሻቸውን እንዳገኘን ይዘን እናቀርባለን።

LEAVE A REPLY