በአማራ ክልል ከ313 ሺሕ በላይ ተፈናቃይ ወገኖች ወደ ቀያቸው እንደተመለሱ ተገለፀ

በአማራ ክልል ከ313 ሺሕ በላይ ተፈናቃይ ወገኖች ወደ ቀያቸው እንደተመለሱ ተገለፀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአሸባሪው የሕወሃት ከተፈናቀሉት ውስጥ እስካሁን ከ313 ሺሕ በላይ ወገኖች ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ እያሱ መስፍን ቡድኑ በወረራ በቆየባቸው አካበቢዎችም ከ2 ነጥብ 3 ሚሊየን የሚበልጥ ሕዝብ ከቤት ንብረቱ በማፈናቀል ለከፋ ችግር እንዲጋለጥ ማድረጉን አስረድተዋል።ከ7 ሚሊዮን የሚበልጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ደግሞ አካባቢያቸውን ሳይለቁ በሽብር ቡድኑ ምክንያት ለተለያዩ ችግሮች ተዳርገው መቆየታቸውንም አመልክተዋል።

በአሁኑ ወቅት ግን አካባቢዎቹ ነፃ መውጣታቸውን ተከትሎ በደብረ ብርሃን፣ ሞጣ፣ መካነ ሰላም፣ ባህር ዳር፣ እብናትን ጨምሮ በሰባት ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎችና ከዘመድና ከህብረተሰቡ ጋር ተጠግተው የቆዩ ተፈናቃይ ወገኖች ወደቄያቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

እስከሁን በተደረገው ጥረት 163 ሺሕ ተፈናቃዮች መንግስት ትራንስፖርት በማመቻቸት ከ150 ሺሕ የሚበልጡት ደግሞ በራሳቸው መመለሳቸውን አስታውቀዋል።

የተመለሱትም በአብዛኛው መጠለያ ያላቸው ሲሆኑ የተጎዳባቸውም ባሉበት መልሶ ለማቋቋም ጥረት እየተደረገ መሆኑም ተመልክቷል።

የቀሩ ተፈናቃዮችንም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ወደቀደመ ቀያቸው ለመመለስ እየተሰራ ነው ያሉት ኃላፊው ተመላሾች የዕለት ምግብ ይዘው እንዲሄዱም ድጋፍ በመደረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY