“ሕዝበ ክርስቲያኑ ታላቁን የዐብይ ፆም ሲፆም የተቸገሩ ወገኖቹን በማሰብ  ሊሆን ይገባል –...

“ሕዝበ ክርስቲያኑ ታላቁን የዐብይ ፆም ሲፆም የተቸገሩ ወገኖቹን በማሰብ  ሊሆን ይገባል – “

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ 

ከሰኞ መጋቢት ፪ቀን፪ሺ፩፮ የሚጀመረውን የአብይ ፃምን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ  መልዕክት አስተላለፉ።

ሕዝበ ክርስቲያኑ የዐብይ ፆም ወራትን የተቸገሩ ወገኖቹን በማሰብ እና በጎ ምግባራትን በማከናወን ሊያሳልፍ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አሳሰበዋል። 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ መጋቢት ፪ቀን፪ሺ፩፮ የሚጀምረውን የዐብይ ፆምን በማስመልከት መልእክት አስተላልፈዋል። 

ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት መልዕክትም፤ ጾም ኃጢአትንና ዲያብሎስን እንዴት እንደሚያሸንፍ ጌታችን እኛን ያስተማረበት ነው  ፆም ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑን የጠቀሱት ፓትርያርኩ፤ ሕዝበ ክርስቲያኑም በዐብይ ፆም ወራት በጎ ምግባራትን በማከናወን በተግባር ሊተረጉመው ይገባል ብለዋል።

ሕዝበ ክርስቲያኑ ታላቁን የዐብይ ፆም ሲፆም በተለያየ ምክንያት የተቸገሩ ወገኖቹን በማሰብ እና ያለውን በማካፈል ሊሆን እንሚገባም አሳስበዋል።

LEAVE A REPLY