የፕሪቶርያውን ስምምነት የሚገመግመው ስብሰባ ተጀመረ

የፕሪቶርያውን ስምምነት የሚገመግመው ስብሰባ ተጀመረ

በኢትዮጵያ መንግስት እና በህውሃት መካከል  በፕሮቶርያ የተደረስውን የተከስ አቁምና የሰላም ስምምነት አፈፃፀምን የሚገመግመው ስብሰባ ዛሬ መጋቢት2/2016 በአፍሪካ ህብረት ፅህፈት ቤት ተጀመረ።

እስከ ዕሮብ መጋቢት 4/2016 ይዘልቃል ተብሎ የሚገመተውን ስብሰባ በንግግር የከፈቱትየአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ማሃማት “እስካሁን የተመዘገቡት የማይካዱ ስኬቶች ቢኖሩም፣ የፖለቲካ ውይይት፣ የሽግግር ፍትሕ እና ትጥቅ የማስፈታት ሂደት፣ ማፈናቀልና መልሶ ማቋቋም አስቸኳይ ትኩረት ከሚሹ ጉዳዮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ብለዋል።

 በዚሁ በዝግ መካሄድ በጀመረው ስብሰባ ላይ የሠላም ሂደቱን የሚቆጣጠረው የቡድኑ አባል እና የአፍሪካ ህብረት ልዩ ልዑክ ኦሌሴጉን ኦባሳንጆ፣ የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት  ኡሁሩ ኬንያታ እና በአፍርካ ቀንድ የአሜሪካ መንግስት ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር  እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ተገኝተዋል።

የፌደራል መንግስት የልዑካን ቡድን  የፍትህ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣  የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ድህንነት እማካሪው አቶ ሬድዋን ሁሴን፤  እና ትጥቅ ማስፈታት፣ የተሃድሶ እና መልሶ ማቋቋም ኮሚሽን ኃላፊ አምባሳድር ተሾመ ቶጋ እና ሌሎችም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል በትግራይ ክልላዊ መንግስት በኩ ልጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ እና የጊዜያዊው አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ጄኔራል ታደሰ ወረዳ ጎን  የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል እና የልዑካን ቡድኑ መሪ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በስብሰባው ላይ መገኝታቸው ታውቋል። en

LEAVE A REPLY