የትግራይ ባለሀብቶች ከባንኮች ብድርና የዕዳ          እፎይታ ይሰጠን ሲሉ ጠየቁ 

የትግራይ ባለሀብቶች ከባንኮች ብድርና የዕዳ          እፎይታ ይሰጠን ሲሉ ጠየቁ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በትግራይ ክልል  ባለሀብቶች ተገቢውንብድር ከባንኮች እንዲያገኙና የብድር ወለድ የእፎይታ ጊዜን የፌዴራል መንግስት ሊያመቻችልን ይገባል ሲሉ መንግስትን አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠየቁ፡፡

ባለፈው ሳምንት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ከትግራይ የመጡ የህዝብ ተወካዬች ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው የትግራይ ክልል የንግድ ዘርፍ ማኅበራት ተወካይ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ጥያቄ ያቀረቡት።

በጦርነት ወቅት መንግሥት ባንክ በአዋጅ እንዲዘጋ ካደረገ በኋላ በክልሉ ጦርነት እንጂ ምንም ዓይነት የሥራ እንቅስቃሴ ባለመኖሩ መንግሰት ይህንን በመረዳትና ያሉትን ችግሮች ቁጭ ብሎ በማጤን ባለሀብቶቹ የተበደሩትን እዳ ብቻ እንዲከፍሉ መደረግ ይኖርበታል ብለዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የትግራይ የንግድ ማህበረስብን በመወከል የተናገሩት  ተወካይ ባለሀብቶቹ ከተበደሩት ብድር ውጪ ወለድ ክፈሉ መባሉ አግባብ እንዳልሆነ ገልጸው፣ ወለዱን ጨምሮ የብድር ክፍያ የጊዜ ገደብና ሌሎች ነገሮች እንዲቀሩ ለብሔራዊ ባንክና ለገንዘብ ሚኒስቴር ደብዳቤ ማስገባታቸውን አስታውሰውከዚህ በፊት በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ባለሀብቶች ብድር እንዲከፍሉ ትዕዛዝ መቀመጡ  ተገቢ አይደለም ያሉት የንግዱ ማህበረሰብ ተወካይ ጊዜውም በጣም አጭር በመሆኑ ሌላ ተጨማሪ ጊዜ እንዲጨመርላቸው መንግስትን ጠይቀዋል።

መጋቢት 6/2016 በጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር በተካሄደ የውይይት መድረክን ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሚመራው ኮሚቴ የወለዱ መጠን ሙሉ ለሙሉ እንዲተው፣ እንዲሁም ባለሀብቶቹ ያለባቸውን ብድር ለመክፈል ሌላ ብድር እንዲመቻችላቸው ጥያቄ መቅረቡንና በያዝነው ሳምንትም ምላሽ እንዲሰጥበት መስማማት ላይ መድረሳቸውን ታውቋል፡፡ en

LEAVE A REPLY