የዓባይ ግድብ  ኃይል ማመንጫ ግንባታ በሰባት ወራት  ይጠናቀቃል

የዓባይ ግድብ  ኃይል ማመንጫ ግንባታ በሰባት ወራት  ይጠናቀቃል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የዓባይ ግድብ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግንባታው በሰባት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የፕሮጀክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ አስታወቁ። 

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ እንዳመለከቱት፤ ቀንና ሌሊት በሚሠሩ ባለሙያዎች አማካኝነት የግድቡ ግንባታ የሲቪል ሥራው 99 በመቶ ተጠናቋል።

ዋናው የግድቡ ክፍል 107 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሌት እንደሚይዝ የተናገሩት ኢንጂነር ክፍሌ፤ ከዚህ ውስጥ አንድ በመቶው ሥራ ብቻ እንደሚቀር አስረድተዋል።

ኢንጂነር ክፍሌ እንዳስታወቁት፤ የግድቡ የኤሌክትሮ ሜካኒካል በተለይም የተርባይንና ጄኔሬተር ተከላ ሥራው 78 በመቶ ተጠናቋል።

እያንዳንዳቸው 375 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሁለት ተርባይን ዩኒቶች በተለያዩ ጊዜያት መገጠማቸውን ያስታወሱት የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ፤ ቀሪ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ተርባይኖች በቀጣይ ወራት ተራ በተራ እየገቡ ይገጠማሉ ብለዋል።

በበርካታ ፈተናዎችና ጫናዎች ሳይበገር ግንባታው የቀጠለው የግድብ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ የኤሌክትሪክ ማመንጫዎቹን ተርባይኖች ሥራ ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ያሉት የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ፤ 

የግድብ የውሃ ማስተላለፊያ አሸንዳዎች ግንባታ ከ85 በመቶ በላይ መድረሱን ኢንጂነር ክፍሌ አመላክተው፤ በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ 95 በመቶ መድረሱን አስታውቀዋል።

የግድብ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግንባታ በሰባት ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ሲሉ ተናግረዋል። en

LEAVE A REPLY