ሩሲያ  በኢትዮጵያ 2,000 የጤና ኬላዎች ልትገነባ ነው 

ሩሲያ  በኢትዮጵያ 2,000 የጤና ኬላዎች ልትገነባ ነው 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በሩሲያ “ሂሮውስ ” በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን ፎር ሜዲካል ስታፍ  የተባለ ተቋም፣ በኢትዮጵያ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እና  መካከል  የሁለትሺ የጤና ኬላዎችን ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በመጋቢት 20 ቀን 2024 መፈራረማቸውን ሩስያ ታይምስ ዘገበ።

የመግባቢያ ሰነዱ በኢትዮጵያ የፓራሜዲካል እና የጽንስና የስነተዋልዶ ጤና ማእከላት የህክምና ባለሙያዎችን በማሰልጠን፣ ስራቸውን በማገዝ፣ የቴሌ መድሀኒት ስርዓትን በመዘርጋት እና በሁለቱ ሀገራት መካከል የጤና አጠባበቅ የህክምና ባለሙያዎች አቅም ለማጎልበት ለ የሚያስችሉ ተግባራትን ላይ  ያተኩራል።

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቶ ጴጥሮስ ወልደጊዮርጊስ እንዳሉት  “በኢትዮጵያ የሚገነቡትን የ2000 የማዋለጃ እና የእናቶችና የህፃናት ጤና ላይ የሚስሩ የጤና ኬላዎችን  ለማንቀሳቀስ የሚጠበቀውን የሰው ሀይል የማዘጋጀት ኃላፊነት አለብን” ብለዋል። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY