ኢትዮጵያ 7ኛውን ወርቅ ሜዳሊያ አገኘች 

ኢትዮጵያ 7ኛውን ወርቅ ሜዳሊያ አገኘች 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በጋና እየተካሄድ ባለው 13ኛው የመላ አፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች እና በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ሩጫ 6ኛውን እና 7ኛውን ወርቅ አግኝታለች፡፡ 

ለኢትዮጵያ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ፍፃሜ በሚያስደምም የአጨራረስ ብቃት ወርቅ ያመጣው አትሌት ሀጎስ ገ/ሕይወት ነው። 

አትሌት ሂሩት መሸሻ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ሩጫ ውድድር የወርቅ ሜዳለያ ያስገኘች ሌላኛዋ ጀግና አትሌት ናት፡፡ አትሌት ሀዊ አበራም  የብር ሜዳሊያ በማስገኝት የአገሯን ክብር ከፍ አስደርጋለች፡፡ በ1500 ሜትር ወንዶች ፍፃሜም ሌላኛው ባለድል ኤርሚያስ ግርማ   የብር ሜዳልያ ለአገሩ አስገኝቷል፡፡ (EN – ኢትዬጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY