በጋምቤላ ፀረሰላም ኃይሎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩ ተገለጸ

በጋምቤላ ፀረሰላም ኃይሎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በጋምቤላ ክልል አልፎ አልፎ እየተከሰተ ያለውን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ   አንዳንድ ግለሰቦች ጎራ እየለዩ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን እያደረሱ መሆኑ ይታወቃል።

ችግር ፈጣሪዎችን በአስቸኳይ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ  የክልሉ መንግስት ከፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ጋር መግባባት ላይ መደረሱን ተከትሎ ነው ኦፕሬሽኑ መካሄድ የተጀመረው።

የፀጥታ ችግሩን ለመቅረፍየኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ የፀጥታ አካላት ወደ ኦፕሬሽን በመግባት ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በቁጥጥር ሥር እያዋሉ እንደሚገኙ ከስፋራው የሚወጡ ዘገባዎች ያስረዳሉ፡፡( EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY